Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 29
Listen to find out how to pay for something at the till.
መክፈያ ቦታ ላይ ክፍያም ስለመፈፀም መናገርን ለማወቅ ይሄንን ያዳምጥ።
Session 29 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
የመክፈያ ቦታ ላይ
Listen to find out how to pay for something at the till.
መክፈያ ቦታ ላይ ክፍያ እንዴት እንደሚፈፀም ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሱቅ ገብተው ለገዙት እቃ ክፍያ ለመፈፀም የሚያስፈልጎትን ቋንቋ ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ሱቅ ውስጥ ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
Shop Assistant
That’s 9.99, please.
Tony
Can I pay with a credit card?
Shop Assistant
Yes. Sign here, please.
Tony
Thank you.
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ የሱቁ ረዳት ለቶኒ ጠቅላላ መክፈል ያለበትን ዋጋ ‘ዘጠኝ ከዘጠና ዘጠኝ ነው’ በማለት ነገረችው። ያስታውሱ፤ ዋጋን የምንገልፀው ከነጥብ በፊት እና በኋላ ያሉትን አሃዞች ነጣጥለን በመናገር ነው። ለምሳሌ ያህል12.99 አስራ ሁለት ከዘጠና ዘጠኝ ሲሆን 20.50 ደግሞ ሃያ ከሃምሳ ነው። ያዳምጡና እና ደግመው ይበሉ።
That’s 9.99, please.
ዘሩባቤል
ከዚያ ቶኖ በክሬዲት ካርድ መክፈል እችላለሁ ‘Can I pay with a credit card?’ ሲል ጠይቋል። በዴቢት ካርድ መክፈል ከፈለጉ ‘Can I pay with a debit card?’ ብለው ይጠይቃሉ። በጥሬ ገንዘብ መክፈል ሲሹ ‘Can I pay with cash?’ ይላሉ። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
Can I pay with a credit card?
ዘሩባቤል
በመቀጠል የሱቁ ረዳት ‘አዎ’፤ እዚህ ላይ ይፈርሙ እባክዎን’ ‘Yes. Sign here, please.’ ብላለች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Yes. Sign here, please.
ዘሩባቤል
ሱቁን ከመልቀቁ በፊት ቶኒ ለሱቁ ረዳት አመሰግናለሁ ‘Thank you’ ብሏል። ይህም ከመሸጫ መደብር ሲወጡ በትህትና የሚሉት ነገር ነው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Thank you.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ሱቅ ውስጥ ሲነጋገሩ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ነገር ያመሳክሩ።
That’s 14.99, please.
Can I pay with cash?
Yes. Here’s your receipt and change.
Thank you.
That’s 19.99, please.
Can I pay with a debit card?
Yes. Sign here, please.
Thank you.
That’s £8.95, please.
Can I pay with a credit card?
Yes. Sign here, please.
Thank you.
ዘሩባቤል
እሽ፥ ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። አሁን እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጣሉ።
That’s 9.99, please.
That’s 9.99, please.
Can I pay with a credit card?
Can I pay with a credit card?
Yes. Sign here, please.
Yes. Sign here, please.
Thank you.
Thank you.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
እርሱ ዘጠኝ ከዘጠና ዘጠኝ ነው።
That’s 9.99, please.
በክሬዲት ካርድ መክፈል እችላለሁ?
Can I pay with a credit card?
አዎ፤ እዚህ ላይ ይፈርሙ እባክዎን።
Yes. Sign here, please.
አመሰግናለሁ።
Thank you.
ዘሩባቤል
ግሩም፤ አሁን ሱቅ ውስጥ ክፍያ መፈፀም እንዴት መጠየቅ እንደሚችሉ አውቀዋል። ከሲያን ጋር ያለውን ውይይት ይለማመዱ። በካርድ መክፈል ይችሉ እንደሆን መጠየቅ እና መደብሩን ሲለቅቁ አመሰግናለሁ ማለቶን ያስታውሱ።
That’s 9.99, please.
Yes, sign here, please.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ንግግር ደግመው ያዳምጡ እና መልስዎን ያመሳክሩ።
Shop Assistant
That’s 9.99, please.
Tony
Can I pay with a credit card?
Shop Assistant
Yes. Sign here, please.
Tony
Thank you.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! አሁን ሱቅ ውስጥ ለዕቃዎች ክፍያ ለመፈፀም የምንጠቀምበትን ቋንቋ አውቀዋል። የተማሩትን መለማመድ አይዘንጉ። ለተጨማሪ የ Essential English Conversation ክፍሎች በሚቀጥለው ዝግጅታችን ይጠብቁን። Bye!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
At the till
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ስለትክክለኛው የቃላት ቅደም ተከተል ያስቡ።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
እኔ እየጠየቅኩ እንደሆነ እና በአንድ ክሬዲት ካርድ እየከፈልን መሆኑን ያስታውሱ።Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ይሄ አዎ ወይንም አይደለም ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው።Question 3 of 3
Excellent!Great job!Bad luck!You scored:
Join us for our next episode of Essential English to learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያንን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
That’s ______, please.
ዋጋው ______ ነው እባክዎ።
Can I pay with a debit card?
በክሬዲት ካርድ መክፈል እችላለሁ?
Can I pay with a credit card?
በክሬዲት ካርድ መክፈል እችላለሁ?
Can I pay with cash?
በጥሬ ገንዘብ መክፈል እችላለሁ?
Yes. Sign here, please.
አዎ፤ እባክዎ እዚህ ላይ ይፈርሙ።
Yes. Here’s your receipt and change.
አዎ፤ ደረሰኝዎ እና መልስዎ ይሄው።
Thank you.
አመሰግናለሁ።