Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 18
Listen to find out how to ask for directions.
አቅጣጫን እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
Session 18 score
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
How do I get to...?
Listen to find out how to ask for directions.
አቅጣጫን እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊተዋቸው የማይቻላቸውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ምህረትእባላለሁ። በዚህ ክፍል በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ ወደተለያዩ ቦታዎች እንዴት መሄዴ እንደሚቻል መጠየቅን ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ወደመሸጫ መደብር እንዴት መሄድ እንደሚቻል ሲነጋገሩ ያዳምጡ።
Phil
How do I get to the supermarket?
Sam
Turn left, go straight on, turn right, it’s on Queen Street.
Phil
Thanks!
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያው ተናጋሪ ወደ ‘መሸጫ መደብር’ ‘supermarket’ እንዴት መሄድ እንደሚቻል ነው የጠየቀው። የተጠቀመው የመጠየቂያ መንገድ ‘ወደ . . . እንዴት መሄድ እችላለሁ’ ‘How do I get to…?’ የሚለውን ነው፤ ከዚያም ‘the supermarket’ የሚለውን ሐረግ አክሎበታል። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
How do I get to the supermarket?
ከዚያም ሁለተኛዋ ተናጋሪ አቅጣጫ ሰጥታዋለች፤ በመጀመሪያ ‘ወደግራ እንዲታጠፍ’ ነው የነገረችው። ከዚያም ‘ቀጥ ብሎ መሄድ’ እንዳለበት ‘go straight on’ ነግራዋለች። በመጨረሻም ‘turn right’ ‘ወደቀኝ ታጠፍ’ ብላዋለች። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Turn left.
Go straight on.
Turn right.
ከዚያም ‘የሚገኘው በኩዊን ጎዳና ላይ ነው’ ‘It’s on Queen Street’ ስትል ነግራዋለች። ‘የሚገኘው’ ‘It’s on…’ ካለች በኋላ የጎዳናውን ስም ጨምራለች። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
It’s on Queen Street.
የመጀመሪያው ተናጋሪ ለተደረገለት ትብብር ‘አመሰግናለሁ!’ ‘Thanks!’ ብሏል። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Thanks!
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች አቅጣጫ ሲጠያየቁ ያዳምጡና እርስዎ ያሉትን ያነፃፅሩ።
ፒት ወደ ‘ባንክ’ ‘bank’ መሄድ ይፈልጋል።
How do I get to the bank?
Turn right, go straight on, turn left, it’s on Perth Road.
Thanks!
እሽ፥ አሁን ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገራቱን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ይሰሟቸዋል።
How do I get to the supermarket?
How do I get to the supermarket?
Turn left.
Turn left.
Go straight on.
Go straight on.
Turn right.
Turn right.
It’s on Queen Street.
It’s on Queen Street.
Thanks!
Thanks!
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱት እንመልከት። አረፍተ ነገራቱን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይናገሩ።
ወደመደብሩ የምሄደው እንዴት ነው?
How do I get to the supermarket?
ወደግራ ታጠፍ።
Turn left.
ቀጥ ብለህ ሂድ
Go straight on.
ወደቀኝ ታጠፍ።
Turn right.
የሚገኘው በኩይንስ ጎዳና ላይ ነው።
It’s on Queen Street.
አመሰግናለሁ።
Thanks!
በጣም ጥሩ፤ እሽ አሁን በእንግሊዝኛ እንዴት አቅጣጫ መናገር እና መጠየቅ እንደሚቻል አውቀዋል። ለመጀመሪያው ተናጋሪ ምላሽ በመስጠት፥ አቅጣጫ እየጠየቁ ልምምድ ያድርጉ።
How do I get to the supermarket?
Thanks!
በጣም ጥሩ፤ አሁን መልስዎን ለማመሳከር ጠቅላላውን ውይይት እንደገና ያዳምጡ።
Phil
How do I get to the supermarket?
Sam
Turn left, go straight on, turn right, it’s on Queen Street.
Phil
Thanks!
በጣም ጥሩ። አሁን በእንግሊዝኛ በሚኖሩበት ከተማ አቅጣጫ መጠየቅ እና መናገር ይችላሉ። የተማሩትን መለማምድን ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ስማችሁን መጠየቅና መናገርን ይለማመዱ። ለተጨማሪ የEssential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
How do I get to...?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
መንግዱን ነው እየጠየቁ ያሉት።Question 1 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ይህ ቃል ሁሌም 'straight' ከተባለው ቃል ጋር አብሮ ይሄዳል።Question 2 of 3
Help
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ይህ ቃል አቅጣጫን መቀየር ማለት ነው።Question 3 of 3
Excellent!Great job!Bad luck!You scored:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
How do I get to ______?
ወደ ______ የምሄደው እንዴት ነው?
the supermarket
የገበያ ማዕከሉ/የመሸጫ መደብሩ
the bank
ባንኩ
the post office
ፖስታ ቤቱ
Go straight on.
ቀጥ ብለሽ/ህ ሂጅ/ድ
Turn right.
ወደቀኝ ታጠፊ/ፍ
Turn left.
ወደግራ ታጠፊ/ፍ
It’s on ______.
የሚገኘው በ ______ ላይ ነው።
Thanks!
አመሰግናለሁ።