የኖቤል የሰላም ሽልማት፡ ስድስቱ አወዛጋቢ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች

ከግራ ወደ ቀኝ፤ ባራክ ኦባማ፣ ዐብይ አሕመድ፣ አን ሳን ሱ ኪ፣ ያሲር አረፋት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከግራ ወደ ቀኝ፤ ባራክ ኦባማ፣ ዐብይ አሕመድ፣ አን ሳን ሱ ኪ፣ ያሲር አረፋት

የ2021 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ዛሬ ዓርብ እኩለ ቀን ላይ ይፋ ይደረጋል። ከዚህ ቀደም የኖቤል ኮሚቴ ሽልማት ካበረከተላቸው መካከል አወዛጋቢ የሆኑ ይገኙበታል።

የኖቤል ሽልማት በዓለማችን ከሚሰጡት ግዙፍ እውቅናዎች መካከል አንዱ ነው። የኖቤል ኮሚቴ ስድስት ሽልማቶችን ይሰጣል። እነዚህም የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ሥነ-ልቦና ወይም ሕክምና፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ኢኮኖሚክስ እና ሰላም ናቸው።

የኖቤል የሰላም ሽልማቶች አብዛኛውን ጊዜ ፖለቲካዊ ይዘት ስለሚኖራቸው ከሌሎች የኖቤል ሽልማቶች አንጻር ሲታይ በተገቢነታቸው ዙሪያ አወዛጋቢ ሆነው ቆይተዋል።

የኖቤል የሰላም ሽልማት ከተቀበሉ እና ብዙ ካወዛገቡ አሸናፊዎች መካከል ስድስቱ የሚከተሉት ናቸው።

ባራክ ኦባማ

ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሳሉ የ2009 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸናፊ ሆነዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሳሉ የ2009 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

የቀድሞ አሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የእአአ 2009 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ሲደረግ፤ ኦባማን ሳይቀር ያስደነቀ እና ያስገረመ ነበር።

ኦባማ እአአ 2020 ላይ በጻፉ ግለ ታሪካቸው ላይ የሰላም ኖቤል አሸናፊ መሆናቸውን ሲሰሙ፤ የመጀመሪያ ምላሻቸው "ምን ስላደረኩ?" የሚል እንደነበረ ገልጸዋል።

ኦባማ የሰላም ኖቤል ማሸነፋቸው የተገለጸው ስልጣን ከያዙ ገና በ9ኛው ወራቸው ነበር። ተቃዋሚዎች ውሳኔው የፈጠና እና ጊዜውን ያልጠበቀ ነው ሲሉ ሽልማቱ ለኦባማ መሰጠቱን አጥብቀው ተችተው ነበር።

ኦባማ አሜሪካንን ለሁለት የስልጣን ዘመን በፕሬዝደንትነት ባስተዳደሩበት ዓመታት ጦራቸው በአፋጋኒስታን፣ ኢራቅ እና ሶሪያ ተዋግቷል።

ያሲር አፋት

ያሲር አረፋት ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ይትዛህክ ራቢን እና ከእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሺሞን ፔሬዝ ጋር በጋራ እአአ 1994 ላይ የሰላም ኖቤል አሸንፈዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ያሲር አራፋት ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ይትዛህክ ራቢን እና ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሺሞን ፔሬዝ ጋር በጋራ እአአ 1994 ላይ የሰላም ኖቤል አሸንፈዋል።

በሕይወት የሌሉት የፍልስጤም መሪ የነበሩት ያሲር አራፋት በኦስሎ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ለነበራቸው አስተዋጽኦ፣ ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ይትዛህክ ራቢን እና ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሺሞን ፔሬዝ ጋር በጋራ እአአ 1994 ላይ የኖቤል ሽልማትን ተቀብለዋል።

እአአ 1990 ላይ በኦስሎ የተደረሰው የሰላም ስምምነት በአስራኤል እና ፍልስጤም መካከል ሰላም ያመጣል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር።

በጦርነት ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ለነበራቸው ያሲር አራፋት የኖቤል የሰላም ሽልማት መስጠትን በእስራኤል እና በተቀረው ዓለም ተቃውሞን ቀስቅሶ ነበር።

በእርግጥ የአራፋት ለኖቤል የሰላም ሽልማት በዕጩነት መቅረብ በኖቤል ኮሚቴ አባላት መካከል አለመግባባትን ፈጥሮ ነበር።

የኖቤል ኮሚቴ አባላ የነበሩት የኖርዌይ ዜጋ የሆኑት ፖለቲከኛው ኬር ክሪስቲያንሰን የአራፋት መመረጥን በመቃወም ከኮሚቴ አባልነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው ለቀው ነበር።

አን ሳን ሱ ኪ

አንግ ሳን ሱ ኪ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, አንግ ሳን ሱ ኪ እአአ 1991 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፍ ችለዋል።

አንግ ሳን ሱ ኪ እአአ 1991 ላይ በምያንማር የነበረውን የጦር ሠራዊት አስተዳደር ሰላማዊ በሆነ መልኩ በመታገላቸው የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፍ ችለዋል።

ከ20 ዓመታት በኋላ ግን አንግ ሳን ሱ ኪ የምንያምር መሪ ሳሉ በንሑሃን ሮሂንጃ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን የግፍ ጭፍጨፋ ማስቆም አልቻሉም። በተባበሩት መንግሥታት 'የዘር ማጥፋት' ስለተባለው ጥቃት አንግ ሳን ሱ ኪ ምንም ሳይሉ አልፈዋል።

ይህም በኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዋ ላይ ከፍተኛ ትችትን አስከትሏል። በርካቶችም አንግ ሳን ሱ ኪ ያገኙትን የሰላም ሽልማት እንዲነጠቁ የሚጠይቁ ድምጾች በስፋት ተሰምተዋል። የኖቤል ሽልማቶች ለአሸናፊው ከተሰጡ በኋላ ሽልማቱን ሊነጠቅ አይችልም።

ይ አሕመድ

ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተቀብለው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተቀብለው ነበር

ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተቀብለው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ሽልማት ያገኙት በአትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በድንበር ግጭት ለ20 ዓመታት የዘለውን ጠላትነት ማስቆም በመቻላቸው ነበር።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ሽልማታቸውን ከተቀበሉ ከአንድ ዓመት በኋላ የኮሚቴው ውሳኔ ትክክለኛነት ላይ ጥያቄዎች መነሳት ጀመሩ።

ዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ በትግራይ ለተነሳው ጦርነት፣ ጦርነቱን ተከትሎ ለተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲተች ቆይቷል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በመሚሩት የፌደራሉ መንግሥት እና በህወሓት አማጺያ መካከል እየተደረገው ያለው ጦርነት ከትግራይ አልፎ ወደ አጎራባች ክልሎች ተሸጋግሯል።

በዚህ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለመሞታቸው፤ በሚሊዮ የሚቆጠሩ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እየተነገረ ነው።

ዋንጋሪ ማታይ

ኬንያዊቷ የማኅብረሰብ አንቂ እአአ 2004 ላይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፉ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ናቸው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኬንያዊቷ የማኅብረሰብ አንቂ እአአ 2004 ላይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፉ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ናቸው።

በሕይወት የሌሉት ኬንያዊቷ የማኅብረሰብ አንቂ እአአ 2004 ላይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፉ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ናቸው።

ዋንጋሪ ማታይ ለዘላቂ ልማት፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነበር የኖቤል ሽልማትን ያገኙት።

ይሁን እንጂ የማኅብረሰብ አንቂዋ ሽልማት ጥይቄ ይነሳበት የጀመረው ስለ ኤችአይቪ ኤድስ የሚሰጡት አስተያየት መሰማት ከጀመረ በኋላ ነበር።

ዋንጋሪ ማታይ ኤችአይቪ ቫይረስ ጥቁሮችን ለማጥፋት ሆነ ተብሎ በላብራቶሪ የተሰራ ቫይረስ ነው የሚል አስተሳሰብን ያራምዱ ነበር።

የዋንጋሪ ማታይን ሃሳብን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ሳይነሳዊ ማረጋገጫ ግን የለም።

ሪ ኪሲን

ሄንሪ ኪሲንጀር (ቀኝ) እና ሌ ደክ ቶ (ግራ እጃቸውን ያነሱት) በጋራ እአአ 1973 ላይ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ነበሩ። ይሁን እንጂ የቬትናሙ ዜጋ ሽልማቱን ለመቀበለ ፍቃደኛ አልነበሩም።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሄንሪ ኪሲንጀር (ቀኝ) እና ሌ ደክ ቶ (ግራ እጃቸውን ያነሱት) በጋራ እአአ 1973 ላይ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ነበሩ። ይሁን እንጂ የቬትናሙ ዜጋ ሽልማቱን ለመቀበለ ፍቃደኛ አልነበሩም።

እአአ 1973 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሄንሪ ኪሲንጀር የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ነበሩ።

ኬሲንጀር ብዙ ተቃውሞ እና ትችት ያስተናገደውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን አስፈጽመዋል። በካምቦዲያ የቦምብ ጥቃት እንዲፈጸም አድርገዋል። በደቡብ አሜሪካ ለአምባገነን የጦር መሪዎች ድጋፍ መስጠታቸውም ሌላው የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩን ካስተቻቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።

ኪሲንጀር የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያገኙት ከሰሜን ቬትናም መሪ ሌ ደክ ቶ ጋር በመሆን የቬይትናም ጦርነት እንዲቆም የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ጥረት በማድረጋቸው ነው።

ለኪሲንጀር የኖቤል የሰላም ሽልማት መሰጠት የለበትም በሚል ሁለት የኖቤል ኮሚቴ አባላት ሥራቸውን ለቅቀው ነበር።

የኪሲንጀር አሸናፊነት ይፋ ሲደረግም፤ ኒው ዮር ታይምስ ሽልማቱን "ኖቤል ዎር ፕራይዝ" ሲል ጠርቶት ነበር።

መሃመ ጋንዲ

መሃተመ ጋንዲ ከሁለት የልጅ ልጆቻቸው ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, መሃተመ ጋንዲ ከሁለት የልጅ ልጆቻቸው ጋር

የኖቤል ሽልማት ለሚገባው ግለሰብ ሳይሰጥ ቀርቷል በሚልም ሽልማቱን በሚሰጥ ኮሚቴ ላይ ቅሬታ ሲነሳ ቆይቷል።

በሰላም ዘረፍ፤ የኖቤል ሽልማት የሚገባቸው ግን ሽልማቱን አላገኙም ተብሎ ስማቸው በተደጋጋሚ ከሚነሱት መካከል መሃተመ ጋንዲ ዋነኛ ናቸው።

ሕንዳዊው ሰላማዊ ታጋይ፤ በተደጋጋሚ ለሽልማቱ ቢታጩም አሸናፊ ሆነው ግን አያውቅም።

እአአ 2006 ላይ የታሪክ ምሁሩ እና የኖበል የሰላም ኮሚቴ ፕሬዝደንት ጊኤር ሉንደስታድ፤ ለጋንዲ አበርክቶዎች እውቅና ሳይሰጥ መቅረቱ በኖቤል የሰላም ታሪክ ውስጥ ትልቁ ክፍተት ነው ብለው ነበር።