ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ተመራማሪዎች በቻይና ዉኃን ግዛት ከለይቶ ማቆያ ወጡ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የኮሮና ተህዋሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ተገኘባት የቻይናዋ ዉሃን ከተማ ለምርመራ ያቀናው የዓለም ጤና ድርጅት የመርማሪዎች ቡድን ከለይቶ ማቆያ መውጣቱ ተገለፀ።
ተመራማሪዎቹ የምርምር ተቋማት ሰራተኞችን፣ ሆስፒታሎችን እና ተህዋሲው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘበት የባህር ምግቦች መሸጫ ስፍራ የሚነግዱ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ ተብሏል።
ይኹን እንጂ የእነዚህ ባለሙያዎች የምርመር ስራ የሚወሰነው የቻይና ባለሥልጣናት በሚሰጡት መረጃ ላይ ነው ተብሏል።
ይህ የሆነው በቻይናና እና በዓለም ጤና ድርጅት መካከል ወራትን የፈጀ ድርድር ከተካሄደ በኋላ ነው።
በኮቪድ-19 ምከንያት ዘመዶቻቸውን ያጡ የተወሰኑ ግለሰቦች የመርማሪ ቡድን አባላቱን ለማግኘት ተስፋ አድርገዋል።
13 የባለሙያዎችን የያዘው ይህ ቡድን ዉሃን የደረሰው ከ14 ቀናት በፊት ነበር። አባላቱ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው ሀሙስ እለት ወጥተዋል። በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩት ባለሙያዎች ከቻይና ተመራማሪዎች እና እርስ በእርሳቸው በቪድዮ ሲወያዩ ነበር።
ሐሙስ ከሰዓት ራሳቸውን ለይተው ካቆዩበት ሆቴል በመውጣት ጋዜጠኞችን ሳያነጋግሩ አውቶቡስ ተሳፍረዋል። ቀደም ብሎ የቡድኑ አባላት ከሆኑት መካከል የተወሰኑት በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበራቸው ጊዜ መጠናቀቅን አስመልክተው፣ ከመንግሥት የተሰጣቸውን የምስክር ወረቀት ጨምሮ በትዊተር ገጻቸው ላይ ለጥፈው ነበር።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2

የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎቹን ወደ ቻይና ከላከ በኋላ አንድ የቡድኑ አባል እንዳይገባ በመደረጉ እንዲሁም ሌሎቹ በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በመስተጓጎላቸው ወደ ቻይና እንዳይገቡ ተከለከሉ ሲል ገልጾ ነበር።
በኋላ ግን የቻይና መንግሥት ስህተቱ የተፈጠረው ይኹነኝ ተብሎ አለመሆኑን ገልጿል።
ኮቪድ-19 በ2019 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በዉሃን ግዛት ሲሆን፣ ቻይና ግን ለበርካታ ወራት ተህዋሲው የተነሳበት ስፍራ ይህ አይደለም ስትል ቆይታ ነበር።
የቻይና መገናኛ ብዙኀን በቅርቡ ወረርሽኙ ከቻይና ውጪ በስፔን፣ ጣልያን ወይንም በአሜሪካ መነሳቱንና ወደ ቻይናም በቅዝቃዜና በታሸጉ ምግቦች ወደ ቻይና ሳይገባ አልቀርም የሚል ዘገባ ሰርተዋል።












