ፋሮ ደሴቶች፡ በባህር ውስጥ የተገነባው አስደናቂው አደባባይ

በዴንማርክ ውስጥ የምትገኘው ራስ ገዟ የፋሮ ደሴቶች በባህር ውስጥ ስትሰራ የነበረውን የመኪኖች መተላፊያ ዋሻዎችና አደባባይ ግንባታ አጠናቃለች። የግንባታ ስራውም ሶስት አመታትን ወስዷል።

የባህር ውስጡ የመኪኖች መተላለፊያ ዋሻዎች ስትሪይሞይና ኤይስቱሮይ የተባሉ ደሴቶችን የሚያገናኙ ሲሆን አስራ አንድ ኪሎ ሜትር እርዝማኔ አላቸው ተብሏል።

ይህ መንገድም ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለመኪኖች ክፍት ይሆናል።

በዋነኝነት እነዚህን መተላለፊያ ዋሻዎች መገንባትም ያስፈለገበት ምክንያት ነዋሪዎች በቀላሉ ከአንዱ ከተማ ወደ አንዱ ከተማ በአጭር ሰዓት እንዲጓዙ ነው።

ከዚህ ቀደም ከመዲናዋ ቶርሻቫን ወደ ሌላኛዋ ከተማ ሩናቪክ ለመድረስ አንድ ሰዓት ከሩብ ይወስድ የነበረው መንገድ በአዲሱ የባህር ላይ ዋሻ 16 ደቂቃዎችን ብቻ ይፈጃል።

የአደባባዩ እይታ

የፎቶው ባለመብት, Estunlar.fo

ዝቅተኛው የዋሻዎቹ መተላለፊያ ከባህር ወለል በታች 187 ሜትር ነው

ዋሻዎች

የፎቶው ባለመብት, Estunlar.fo

የመተላለፊያ ዋሻዎቹም ደህንነትም በደንብ ተጠንቶበት እንደተሰራ ግንባታውን የተቋረጠው ኩባንያ አስታውቋል።

የዋሻው መግቢያ

የፎቶው ባለመብት, Estunlar.fo

ዋሻዎቹም ሆነ አደባባዩ አገልግሎት ከመስጠታቸው በፊት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ያካተተ ቡድን ሙከራውን ቀድሞ እንደሚያከናውን የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋልል።

በዋሾቹ መሃል የተገነባው አደባባይም የደሴቲቷን አርቲስት ትሮንዱር ፓቱርሰን የጥበብ ስራዎች ይንቆጠቆጣል። የሃውልት ሰራዎችን ጨምሮ ውብ የሆኑ መብራቶችም ይኖሩታል።

ዋሻው ላይ አንድ ሰራተኛ ቀለም ሲቀባ

የፎቶው ባለመብት, Estunlar.fo

በዋሻው መተላለፍ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ገንዘብ መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህም አንዴ ለሚያልፉበት 9 ፓውንድም እንደሆነ የአገሪቱ ድረገፅ አስፍሯል። ክፍያቸውን ተመዝግበው ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ ወይም አመታዊ የሚያደርጉት ከሆነ ረከስ ይልላቸዋል።

የአንደኛው ዋሳ መግቢያ

የፎቶው ባለመብት, Estunlar.fo

የግንባታው ተቋራጭ ኤንሲሲ እንደሚለው ከሆነ እነዚህ መተላለፊያ ዋሻዎች ደሴቲቷ እስካሁን ድረስ ለመሰረተ ልማት ብላ ካወጣችው ገንዘብ ከፍተኛ እንደሆነ ነው።

የዋሻው እይታ

የፎቶው ባለመብት, Estunlar.fo

በአሁኑ ወቅትም ሳንዶይና ስትሪይሞይ የተባሉ ደሴቶችን ለማገናኘትም ሌሎች መተላለፊያ ዋሻዎች እየተገነቡ ነው።

የፋሮ ደሴቶች፣ በሰሜን አትላንቲክ አገራት በአይስላንድና በኖርዌይ መካከል የምትገኝና 18 ደሴቶችን የያዘች ሲሆን፤ በዴንማርክም ውስጥ የምትገኝ ራሰ ገዝ አስተዳደር ናት።