በመቀለ ከተማ አንዲት ሴት ከሚሊሻ በተተኮሰባት ጥይት ተገደለች

መቀለ ከተማ

የፎቶው ባለመብት, EDUARDO SOTERAS

የምስሉ መግለጫ, መቀለ ከተማ

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ አንዲት ሴት ከታጣቂ ሚሊሻ በተተኮሰባት ጥይት መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ።

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ ትናንት ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት አንዲት ሴት ከታጣቂ ሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት መገደሏን የመቀለ ከተማ ወንጀል መከላከልና ምርመራ ፅ/ቤት ለቢቢሲ ገልጿል።

ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በስም ያልተጠቀሱት ግለሰቦቹ በሥራ ክፍያ ሳይስማሙ ቀርተው አለመግባባታቸው ተባብሶ ታጣቂው ተኩሶ ገድሏታል።

ታጣቂው በተኮሰባት ጥይት የተመታቸው ሴት፤ ህይወቷ ወዲያውኑ አልፏል ብሏል ፖሊስ። ታጣቂው ግድያውን ከፈፀመ በኋላ ራሱ ላይ በመተኮሱ ለጉዳት ተዳርጎ ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዱን እና በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ተደርጎለት በፖሊስ ጥበቃ ሥር ሆኖ ህክምና እየተከታተለ እንደሚገኝ ፅ/ቤቱ አስታውቋል።