ዋትስአፕ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ስልኮች ላይ መስራቱን አቆመ

የፎቶው ባለመብት, GETTY IMAGES
ከዛሬ ጀምሮ የመልዕክት ማስተላላፊያው የዋትስአፕ መተግበሪያ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ስልኮች ላይ ሥራ አቁሟል።
ቀኑ ያለፈበትን የመተግበሪያ የሚጠቀሙ አንድሮይድና አይፎን ስልኮች በፌስቡክ ባለቤትነት ስር ኣለውን ዋትስኣፕን መጠቀም የሚያስችሉ ስልኮች አይደሉም ተብሏል።
ዋትስፕ እንደሚለው የተጠቃሚዎቹን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ይህን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
አንድሮይድ 2.3.7 የሚጠቀሙ ስማርት ስልኮች ከአይፎን ደግሞ iOS 8 እና ከዚያ በፊት የተመረቱ ከሆኑ ዋትስኣፕ መጠቀም አያስችሉም።
አሁን ዋትስአፕ ያቋረጠውን አገልግሎት የሚሰጡት መተግበሪያዎች በሌላ አዲስ ስልክ ላይ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ወይም አቅማቸው ማደግ የማይችል ናቸው።
አብዛኛዎቹ ተጠቃሚዎች የተሻሻለውን መተግበሪያ ለማግኘትና መልዕክት አገልግሎቱን ለመጠቀም እዚያው ላይ ማሻሻል (አፕዴት) ማድረግ ይችላሉ።
ቢሆንም ግን የተወሰኑ ስልኮች ለአብነት እንደ አይፎን 4s ያሉ ሆነው iOS 7 ብቻን የሚጠቀሙ ግን መተግበሪያውን አይቀበሉም።
"ዋትስአፕ የተለየ ምርጫ የለውም፤ ያለው ምርጫ የደንበኞቹን ደህንነት ማረጋገጥ ነው። ይህ በእርግጥ የእራሱ የሆነ ጉዳት አለው። በርካታ አሮጌ ስልኮች መተግበሪያውን አይቀበሉም" ብለዋል ተንታኙ ቤን ውድ።
ዋትስአፕ በ10 ዓመቱ በከፍተኛ ደረጃ ከኢንተርኔት የተጫነ መተግበሪያ ነው። አሁን የሚደረገው ለውጥ ከሁለት ዓመት በፊት እንዲደረግ ደንበኞች አስጠንቅቀው ነበር።
"ይህ ለእኛ አስቸጋሪ ውሳኔ ነበር፤ ነገር ግን ደንበኞች ከጓደኞቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ደህንነት ተሰምቷቸው በዋትስአፕ እንዲጠቀሙ እንፈልጋለን" ብለዋል የኩባንያው ቃል አቀባይ።
ይህ የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያው በ2016 ከብዙ ስልኮች ላይ መሥራት ማቋም በኋላ ከተወሰደው እርምጃ የቀጠለ ነው።












