'ወንድ ያገቡት' ኡጋንዳዊ ኢማም ከኃላፊነታቸው ታገዱ

ሙሽሪትና ሙሽራው

የፎቶው ባለመብት, The Daily monitor

'ሴት ናት' ሲሉ በማሰብ ወንድ ያገቡት ኡጋንዳዊው ኢማም ከኃላፊነታቸው መታገዳቸውን ዘ ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ ዘገበ።

ሼህ ሞሃመድ ሙቱምባ ለሁለት ሳምንታት አብራቸው የቆየችውና 'ሴት ናት' ሲሉ ያገቡት ሂጃብ ለባሹ 'ሚስታቸው' ስዋቡላህ ናቡኬራ፤ ወንድ እንደነበረ ባወቁ ጊዜ በድንጋጤ ደርቀዋል።

የአሁኗ 'ሙሽሪት' የቀድሞ ስሙ ሪቻርድ ቱሙሻቤ እንደነበር ተዘግቧል።

እውነታው የተረጋጋጠው 'ባለቤታቸው' ቱሙሻቤ፤ አዲስ ትዳር በመሰረተችበት ቤት አካባቢ ከሚኖሩ ጎረቤቶቿ የቴሌቪዥን ማስቀመጫና ልብሶችን በመስረቅ ተጠርጥራ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ነበር።

"በተለመደው የፖሊስ ሥራ መሠረት፤ ሴት ፖሊስ እርሷን ወደ እስር ቤት ክፍል ከማስገባቷ በፊት ፍተሻ አድርጋ ነበር፤ ከዚያ ግን የሆነው ፖሊሷንም ድንጋጤ ውስጥ የከተተ ነበር፤ ተጠርጣሪው ጡት እንዲመስል በጡት መያዣ ጨርቆችን በመጠቅጠቅ ለብሶ ተገኝቷል" ሲል ጋዜጣው አትቷል።

ከአገሪቷ ዋና መዲና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ክያምፒሲ በተባለች መንደር በሚገኝ መስጊድ ኢማም የሆኑት ሼህ ሙቱምባ፤ በነበሩት ጊዜያት 'ከሙሽራቸው' ጋር ወሲባዊ ግንኙነት አልነበራቸውም።

እንዴት ከሙሽራቸው ጋር ወሲባዊ ግንኙነት አልፈፀሙም ይሉ ይሆናል። ምክንያቱ ወዲህ ነው "ሙሽሪት የወር አበባ ላይ ነኝ" በማለቷ ነበር ግንኙነት ሳያደርጉ የቆዩት።

ጋዜጣው እንዳስነበበው 'ግለሰቡ' ያለፆታው ሴት ለመምሰል በመሞከር፣ በስርቆት እና በማስመሰል የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመቀበል ክስ ተመስርቶበታል።

የአካባቢው ካዲ [የእስልምና ዳኛ] ሼህ አብዱል ኑር ካካንዴ በበኩላቸው አጋጣሚው ያልተጠበቀ ሲሆን በኢማሙ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

ጋዜጣው ሼህ ሙቱምባ በሚያስተምሩበት መስጊድ ዋና ኢማም የሆኑትን ሼህ ኢሳ ቡሱልዋን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስልምና ኃይማኖትን ለመጠበቅ ሲባል ኢማሙ ከኃላፊነታቸው ታግደዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

አክሎም ሼህ ሙቱምባ ላለፉት አራት ቀናት ቤታቸው አልነበሩም ብሏል- ጋዜጣው።

"በተፈጠረው ስሜታቸው በጣም ተጎድቷል፤ በመሆኑም የምክር አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል" ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብም ተናግረዋል።