በምዕራብ ቨርጂንያ የማረሚያ ቤት እጩ ጠባቂዎች ባሳዩት የሰላምታ አይነት ተባረሩ

Employees at the West Virginia Division of Corrections and Rehabilitation giving the salute below a sign that reads "HAIL BYRD!"

የፎቶው ባለመብት, West Virginia Department of Military Affairs

የምስሉ መግለጫ, ፎቶውን በምርቃት ቀናቸው ላይ ነው የተነሱት

በትንሹ 30 የሚሆኑ የማረሚያ ቤት እጩ ሰልጣኞች በምረቃ ቀን ፎቶግራፋቸው ላይ ያሳዩት የናዚን ምልክት የሚመስል ሰላምታቸው ለመባረር ዳርጓቸዋል።

የምዕራብ ቨርጂንያ የማገገምያ እና ማረምያ ክፍል ሰልጣኞች የናዚውን ሰላምታ በሚያሳያው ምስል ላይ የአስተማሪያቸውን ስም "ሃይል ባይርድ" በማለትም ተጠቅመውበታል።

ሰኞ ዕለት የግዛቱቲቱ ገዢ እጩ ሰልጣኞቹ ሊባረሩ ይችላሉ ሲሉ አሰታውቀዋል። ፎቶውን የተነሱትም ባለፈው ወር ላይ ነበር።

"ከመጀመርያው እንደተናገርኩት የ 18ኛው ክፍል ሰልጣኞች ፎቶ ባለው ጠንከር ያለ መልእክት አወግዘዋለው" ያሉት ገዢው "ይህ አይነት ባህሪ በመንግሰት አካላት በትግስት የሚታለፍ አይደለም ሲሉም አክለዋል።

በፎቶው ላይ ከታዩት በተጨማሪም ሁለት አሰልጣኞች እና አንድ ሌላ ሰልጣኝም ቀደም ሲል ተባረዋል።

ምስሉ የ30 ሰዎችን ፊት ደብዘዝ አድርጎ ያሳያል፤ ምስሉም የ18ኛ መሰረታዊ ስልጠና ክፍል ነው። የሰራተኞቹን ስምና የት እደተነሱት አይገልፅም።

አንድ የክፍሉ ሰራተኛ ምስሉን ከተቀበለ በኋላ ነገሩ እንዳሳሰበው ለስልጠና ክፍል ሀላፊዋ አሳወቆ ነበር። ሆኖም ሀላፊዋ ፎቶው ምንም ችግር የለውም ስትል እንደመለሰችው ተገልጿል።

በምስሉ ላይ ይህንን አይነት ምልክት ያሳዩት ''እኔ እንደ ሂትለር ጠንካራ ስለሆንኩኝ ነው"ስትልም ተናግራለች።

ስለተባረሩት ሰልጣኞች ስም ግን ምንም የተባለ ነገር የለም።