ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለማህጸን ለካንሰር መከላከያ ክትባት ከሚሰጡ ጥቂት አገራት አንዷ ናት

አንጀሊን ኡሳናሴ ከየማህጻን በር ጫፍ ካንሰር የዳኑ
የምስሉ መግለጫ, አንጀሊን ኡሳናሴ ከየማህጻን በር ጫፍ ካንሰር የዳኑ

የማህጻን በር ጫፍ ካንሰር በመላው ዓለም ለሴቶች ሞት ምክንያት ከሆኑት የካንሰር አይነቶች መካከል አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በአፍሪካ ግን ይህ በሽታ ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በተለየ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ ገዳይ ነው፤ ምንም እንኳ ቀድሞ መከላከል ቢቻልም።

በሩዋንዳ የተጀመረው በሽታውን የመከላከል እንቅስቃሴ ውጤትማ መሆኑን ተከትሎ ሌሎች የአፍሪካ አገራት የሩዋንዳን ተመሳሌት መከተል ጀምረዋል።

አንጀሊን ኡሳናሴ በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ትኖራለች። የ67 ዓመት አዛውንቷ አንጀሊን በማህጻን በር ጫፍ ካንሰር ህይወቷ እንዴት እንደተቀየረ ታስታውሳለች።

ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ነበር ድንገት በሙታንታዋ ላይ ደም የተመለከተችው። የ67 ዓመት ሴት መቼም የወር አበባ ልታይ አትችልም። እንዲህ አይነት ምልክት በእራሷ ላይ ካየች ዓመታት አልፈዋል።

"በአቅራቢያዬ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሄድኩኝ። ከዚያም ሃኪሞች የማህጻን በር ጫፍ ካንሰር ምረመራ እንዳደርግ ነገሩኝ። የምረመራ ውጤቱ ሲመጣ በሽታው እንዳለብኝ አሳየ። በጣም ተደናገጥኩ። ልቀበለው አልቻልኩም። የምሞት መሰለኝ" በማለት የነበረውን ሁኔታ ታስታውሳለች።

አንጀሊን በሽታውን በጊዜ ማወቋ እና የህክምና ዕርዳታ ማግኘቷ ህይወቷን እንደታደረገው ታምናለች።

📝
Frequently asked questions
ስለኤችፒቪ ማወቅ ያለብዎ ነገሮች
የበለጠ ለማወቅ ጥያቄዎቹን ይጫኑ
1. ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (ኤችፒቪ) ምንድን ነው?
2. ልያዝ እችላለሁ?
There is an Infographic showing the risk factors that are related to HPV such as sex, substance abuse, reproductive health, body composition, infections and puberty
3. አደገኛ ነው?
There is an infographic showing how HPV causes cancer. When HPV infection occurs, the virus may remain dormant or cause warts or damage DNA hence causing cancer
4. የማህጸን በር ካንሰር በምኖርበት አካባቢ ምን ያህል አደገኛ ነው?
There is a map showing incidence and mortality rates in women around the world. It is noted that death rates of women in Africa are higher than anywhere else
5. እነማን ናቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠቁት?
አፍሪካ ውስጥ ያሉ ሴቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅተዋል

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት በየዓመቱ ከ100ሺህ በላይ ሴቶች የማህጸን በር ካንሰር በምርመራ የሚገኝባቸው ሲሆን፤ ህክምና ካላገኙ ከአስሩ ስድስቱ ይሞታሉ።

ስለበሽታው ያለ ዝቅተኛ ግንዛቤና አቅምን ያገናዘበ ህክምና አለመኖር የአፍሪካ አገራትን የበሽታው መናኽሪያ አድርጓቸዋል። አፍሪካውያን ሴቶች ከሌሎች አህጉራት አቻዎቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ፣ ለእነዚህ የካንሰር አይነቶች ያሉ ምርመራዎችና ህክምናዎችን የማግኘት ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው።
6. ከኤችፒቪ ራሴን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እችላለሁ?
የተሳተፉ
ዝግጅት፡ ፒዩሪቲ ቢሪር፣ ዲዛይን፡ ሚሊ ዋቺራ፣ አኒሜሽን፡ ጆርጅ ዋፉላ፣ ጥናትና ጽሁፍ፡ ሺላ ኪማኒ፣ አንተኒ ማኮኻ፣ Anthony Makokha, አዘጋጅ፡ ሁጎ ዊሊያም፣ ሙቶኒ ሙቺሪና ሚሊ ዋቺራ

ዛሬ ላይ ቢሆን ግን አንጀሊን ይህ በሽታ ባልያዘት ነበር። ምክንያቱም በመላው ሩዋንዳ የተጀመረው የቅድመ ማህጻን በር ጫፍ ካንሰር ምረመራ እና ክትባት በታደጋት ነበር።

ለማህጻን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ መከሰት በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፈው ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (ኤችፒቪ) አብዛኛውን ጊዜ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል።

ምንም እንኳ በአፍሪካ ይህ በሽታ ከፍተኛ ሞት የሚያስከትል ቢሆንም 10 አገራት ብቻ ናቸው የማህጻን በር ጫፍ ካንሰር ክትባትን ለዜጎቻቸው የሚሰጡት።

ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ተጠቃሽ አገር ናት።

በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 ሃገራት ብቻ ናቸው የማህጻን በር ጫፍ ካንሰር ክትባትን ለዜጎቻቸው የሚሰጡት።

የፎቶው ባለመብት, UNICEF

የምስሉ መግለጫ, በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 ሃገራት ብቻ ናቸው የማህጻን በር ጫፍ ካንሰር ክትባትን ለዜጎቻቸው የሚሰጡት።

በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ አገራት ለዜጎቿ ክትባቱን በብቸኝነት የምታቀርበው ሴኔጋል ናት።

በምሥራቅ አፍሪካ ደግሞ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ለዜጎች ክትባቱን ስለሚያቀርቡ በማህጻን በር ጫፍ ካንሰር የሚከሰተው ሞት ከሌሎች የአህጉሪቱ ቀጠና ጋር ሲነጻጸር ዝቅ ያለ ነው።

ሩዋንዳ ከስምንት ዓመታት በፊት የጀመረችው ዘመቻ አዎንታዊ ውጤት አስገኝቶላታል። ከ10 ሴቶች 9 ሴቶች ክትባቱን ማግኘት ችለዋል።

ይህ ውጤት ግን ያለፈተና አልነበረም የመጣው።

ክትባቱ የሚያስወጣው ከፍተኛ ገንዘብ እስከ ለክትባቱ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች ሩዋንዳዊያን የተሻገሯቸው ጋሬጣዎች ናቸው።

"አሁንም ቢሆን የማህጻን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ እርግማን ነው በማለት ወደ ሃኪም ከማቅናት ይልቅ ወደ ጠንቋዮች ጋር የሚሄዱ ሴቶች አሉ" በማለት አንጀሊን ትናገራለች።

ከዚህ በተጨማሪ በበሽታው ምክያት 'ማህጸናችን እንዲወጣ ሊደረግ ይችላል' የሚለው ስጋት በርካታ ሴቶች ወደ ህክምና እንዳይሄዱ ይገድባቸዋል።

የኤችፒቪ ክትባት በሽታው በወጣቶች መካከል እንዳይስፋፋ በከፍተኛ ደረጃ ያደርጋል

መንግሥት የማኅበረሰብ መሪዎችን፣ አብያተ ክርስቲያናትን፣ የመንደር መሪዎችን፣ የጤና ሰራተኞችን፣ ትምህርት ቤቶችንና የመገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም በክትባቱ ዙሪያ የሚነዙ አፈታሪኮችን ለማስወገድ ዘመቻ አካሂዷል።

ተማሪ ለሆኑት ልጃገረዶች በትምህርት ቤት ለማይማሩት ደግሞ በየቤታቸው ክትባቱን እንዲያገኙ ተደርጓል።

የጤና ባለስልጣናትም ክትባቱ በተፈለገበት ቦታና ጊዜ ሁሉ በበቂ ሁኔታ በፍጥነት እንዲገኝ አድርገዋል።

የኤችፒቪ ክትባት በሽታው በወጣቶች መካከል እንዳይስፋፋ በከፍተኛ ደረጃ ያደርጋል
የምስሉ መግለጫ, የኤችፒቪ ክትባት በሽታው በወጣቶች መካከል እንዳይስፋፋ በከፍተኛ ደረጃ ያደርጋል

ኅብረተሰቡ በስፋት እንዲከተብ የሚያስችለው የመጀመሪያው የክትባት ዘመቻ ከተጀመረ ከስምንት ዓመታት በኋላ ክትባቱ የሩዋንዳ መደበኛ የክትባቶች ዝርዝር ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል።

ምንም እንኳን ሩዋንዳ ያገኘችውን ውጤት የሚያሳይ መረጃ ባይኖርም ተመሳሳይ ዘዴን የተጠቀሙ አገራት ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ የኤችፒቪ በሽታ መስፋፋት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።

አውስትራሊያ ከ1991 (እአአ) ጀምሮ ሴቶች የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማደረግ የተጀመረ ሲሆን ከ12 ዓመት በፊት ደግሞ ክትባቱ መስጠት ተጀምሯል።

የአውስትራሊያ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ክስተት መጠን ከአንድ መቶ ሺህ ሴቶች ሰባት ብቻ ነው፤ ይህም በዓለም ላይ ከሚታየው አማካይ ቁጥር በግማሽ ያመነሰ ነው።

በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ደግሞ ዓመታዊው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር አዲስ ክስተት በአንድ መቶ ሺህ ሴቶች ወደ ስድስት ዝቅ ይላል ተብሎ ይጠበቃል።

'በየቀኑ ዘጠኝ ሴቶች ይሞታሉ'

የሩዋንዳን እርምጃ በመከተል ሌሎች የአፍሪካ አገራት በአሁኑ ጊዜ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ነው።

በጥቅምት ወር የኬንያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ጋር በመተባበር የኤችፒቪ ክትባትን ከመደበኛ የክትባት አይነቶች ጋር እንዲሰጥ ማድረግ ጀምሯል።

በዚህም ዘመቻ እድሜያቸው 10 ዓመት የሆናቸው 800 ሺህ ታዳጊ ሴቶችን በየዓመቱ ለመከተብ ፍላጎት አለው።

"ኬንያ ውስጥ በየቀኑ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምክንያት ዘጠን ሴቶች ይሞታሉ። ይህንንም ለመከላከል ነው ለልጃገረዶች ክትባት ለአዋቂ ሴቶች ደግሞ ምርመራ የሚደረገው" ሲሉ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኘው የአጋ ካን ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ውስጥ የጽንስና የማህጸን ፕሮፌሰር የሆኑት ማርሊን ተመርማን ይናገራሉ።

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የጡት ካንሰር 12 ምልክቶች

ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ የጤና ባለስልጣናት ክትባቱ ካለበት ቀላል የጎንዮሽ ችግር በስተቀር ደህንነቱ የተጠበቀና ውጤታማ እንደሆነ ቢገልጹም አንዳንዶች አሁንም ጥርጣሬ አላቸው።

"ስለክትባቱ የምሰማው ነገር ስላስፈራኝ የአስር ዓመቷ ልጄን እንድትከተብ አላደረግኩም። ሲከተቡ ሽባ ሊሆኑ ወይም የደም መርጋት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል የሚገልጹ ወሬዎች አሉ። ስለክትባቱ ምንም አይነት ትምህርት አልተሰጠንም" የምትለው በኬንያዋ የባሕር ዳርቻ ከተማ ሞምባሳ ነዋሪ የሆነችው እናት ቦንጄ አትማን ናት።

ሃይማኖታዊ ስብስብ የሆነው የኬንያ የካቶሊክ ዶክተሮች ማህበር ግን ክትባቱን ለታዳጊ ልጃገረዶች መስጠት አስፈላጊ አይደለም በማለት ሴቶች ክትባቱን እንዳይወስዱ ጥሪ አቅርቧል። ኤችፒቪንም ለመከላከል ከወሲብ መታቀብ ወይም በአንድ የትዳር አጋር መወሰንን እንደመፍትሄ አቅርቧል።

ሩዋንዳ ውስጥ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰርን ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

"ዘመቻውን በጀመርንበት ወቅት ከፍ ባለ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ክትባቱን አላገኙም ነበር። አሁን ትኩረታችን በ30 እና በ49 እድሜ ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን መመርመር ነው" ይላሉ ዶክተር ኡዊንክዊነዲ።

አንጀሊን ሌሎች ስለበሽታው ያለቸውን ግንዛቤ ለማስፋትና ማግኘት የሚገባቸውን ህክምና እንዲወስዱ ለማበረታታት የራሷን የካንሰር ታሪክ በመንገር ጥረት እያደረገች ነው።

"የምችል ቢሆን ኖሮ፤ ሁሉንም አሰልፌ ምርመራ እንዲያደርጉ ሃኪም ጋር እወስዳቸው ነበር" ትላለች።