ግብፅ ከአሜሪካ ያስመለሰችውን ጥንታዊ የሬሳ ሳጥን ለዕይታ አቀረበች

ግብፅ ከአሜሪካ ያስመለሰቻቸውን ጥንታዊ ቅርሶች ተከትሎ 2100 ዓመታትን ያስቆጠረውን የአንድ ቄስ የአስክሬን ሳጥን ለዕይታ ማቅረቧን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ሬሳ ሳጥኑ ከግብፅ የተዘረፈው በ 'አረብ ስፕሪንግ' አብዮት ወቅት የነበረ ሲሆን ኒው ዮርክ ለሚገኘው ሜትሮፖሊታን ሙዚየም ቅርሱን ሲገዛ፤ ከግብፅ ተዘርፎ የተወሰደ መሆኑን እንዳላወቀ ተገልጿል።
ሙዚየሙ፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እንደተሠራ የሚገመተውን የሬሳ ሳጥን ለግብፅ ባለሥልጣኖች ማስረከቡ የሚታወስ ነው።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2011 ግብፅ ውስጥ አብዮት ሲቀጣጠል፤ ሬሳ ሳጥኑ ሚንያ ከሚባለው አካባቢ ተዘርፎ፤ በዱባይ በኩል ወደ ጀርመን ከዛም ወደ ፈረንሳይ ተወስዷል።
ከዚያም ሀሰተኛ መረጃዎችን በመጠቀም በዓለም አቀፉ የሥነ ጥበብ ደላሎች አማካኝነት አሜሪካ ኒዮርክ ለሚገኘው ሜትሮፖሊታን ሙዚየም መሸጡን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ኔደጅማንክህ የተባሉት እና ሔሪሻፍ የተባለው አማልክት ቄስ የደረቀ አስክሬን እንደሚገኝበት ተገልጿል።
'ኔጀማንክህ' በመባል የሚታወቀው እና በወርቅ የተለበጠው የሬሳ ሳጥን ተሰርቆ በሕገ ወጥ መንገድ ከግብፅ የወጣው በአውሮፓዊያኑ 2011 ነበር።
የአስክሬን ሳጥኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንደኛው ክፍለ ዘመን በ4 ሚሊየን ዶላር ከፐርሺያኖች መገዛቱ ተነግሯል።
ሙዚየሙ 1971 ሐሰተኛ የውጭ ንግድ ፈቃድ እና ሀሰተኛ መረጃዎች እንደቀረቡለት እና ሳያውቁ እንደተገዛ አቃቤ ሕግ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
ባለሥልጣናቱ እንዳሉት ጥንታዊ የሆነው የአስክሬን ሳጥን በአውሮፓዊያኑ 2011 ተሰርቆ እስከሚወሰድ ድረስ በግብፅ ሚንያ ክልል ከ2000 ዓመታት በፊት ተቀብሮ ነበር የቆየው።














