የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሃላፊ ተዘረፉ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ዜጎችን ከዘራፊዎችና ከነጣቂዎች መታደግ የፖሊስ ቀዳሚ ሃላፊነት ቢሆንም ፖሊሶችም እንኳን ለሌላ ለራሳቸው መሆን አቅቷቸው የቀማኛ ሲሳይ የሚሆኑበት አጋጣሚም አልፎ አልፎ አይጠፋም።
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አዛዥ ጀነራል ኬህላ ሲቶልም ያጋጠማቸው ይህው ነው።
ሌቦች ከፖሊስ አዛዡ መኖሪያ ቤት በመግባት ሁለት ቴሌቪዥኖችን ይዘው ጠፍተዋል። ምፑማላንጋ በተኘ ግዛት ውስጥ በግንባታ ላይ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲዘረፍ የፖሊስ አዛዡ ኬፕታወን ውስጥ ነበሩ ተብሏል።
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት መኖሪያ ቤታቸው ሲዘረፍ የፖሊስ አዛዡ እየተበራከተ ያለውን ወንጀል ለመከላከል በሚሰራ ስራ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነበሩ።








