ደቡብ አፍሪካዊያኑ ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን አደረጉ

ደቡብ አፍሪካዊያኑ ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን ከኬፕታውን ወደ ካይሮ ያደረጉ ሲሆን በተሳካ ሁኔታም ለእረፍት ናሚቢያ አርፈዋል።
12 ሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው ይህ በረራን ለማጠናቀቅም ስድስት ሳምንት ይፈጅባቸዋል ተብሏል።
አራት መቀመጫ ያላት ይህች አውሮፕላን ከተለያየ ስፍራ በተውጣጡ 20 ተማሪዎች ነው የተገጣጠመችው።
"የዚህ ፕሮጀክት ዋናው አላማ አዕምሯችንን ይቻላል ብለን ካሳመንነው እንደሚቻል ለአፍሪካዊያን ለማሳየት ነው" በማለት የ17 ዓመቷ ፓይለት ሜጋን ዌርነር ትናገራለች።

ታዳጊዎቹ አውሮፕላኗን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ሳምንታት የፈጀባቸው ሲሆን፤ የውስጥ አካሏን ከደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በመግዛት እንዲሁም በሺህዎች የሚቆጠሩ የውስጥ አካሏን መገጣጠም ችለዋል።
"አውሮፕሏን ሳያት ማመን አልቻልኩም። በጣም ነው የኮራሁት፤ አውሮፕሏኗን ሳያት ልጄን ነው የምትመስለኝ። በጣም ነው የምወዳት" በማለት ከጓተንግ ግዛት የመጣችው የ15 ዓመቷ ኪያሞግትስዌ ሲመላ ገልፃለች።
አክላም "ደስ በሚል ሁኔታ ነው አውሮፕላኗ የምትበረው፤ ዕይታው ልብን የሚሰርቅ" በማለት ከጆሃንስበርግ ኬፕታውን ከበረሩ በኋላ ተናግራለች።
At first people in my community were shocked - they didn't believe me when I told them I helped build a plane... But now they're actually very proud of me"

የአስራ አምስት ዓመቷ አውሮፕላን አብራሪ ይህ ሥራቸው ሌሎችንም እንደሚያነቃቃ ተስፋ አድርጋለች። "በመጀመሪያ የአካባቢው ማህበረሰብ በጣም ደንግጦ ነበር፤ አውሮፕላን ገጣጥመን ከኬፕታውን ካይሮ ልንበር ነው የሚለውን ዜና ማመን ከብዷቸው ነበር" የምትለው ታዳጊዋ ውጤቱን ካዩ በኋላ ግን ኩራት እንደተሰማቸው ተናግራለች።

ይህንን ፕሮጀክት የጀመረችው የ17 ዓመቷ ሜጋን ስትሆን አንድ ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም ባደረጉት ማጣራት20 ተማሪዎች ተመርጠዋል።
የአብራሪነት ፍቃድ ካገኙት ስድስቱ ታዳጊዎች አንዷ ሜጋን ስትሆን፤ ግራጫ ቀለም ያላትንና በስፖንሰሮች አርማ የደመቀችውን አውሮፕላንን የማብረር ኃላፊነቱ በስድስቱም ትከሻ ላይ ወድቋል።
ከየቀኑ ትምህርት በተጨማሪ የአብራሪነት ስልጠናዋን የወሰደችው ሜጋን "የአብራሪነት ፍቃድ ማለት ዲግሪ ማግኘት ማለት ነው" ትላለች።
It's just awesome to see how inspired people are by what we've done"

የአውሮፕላን አብራሪ አባቷ ደስ ዌርነር አራት ሰዎችን የሚይዝ አውሮፕላን ለመገጣጠም ሦስት ሺ ሰዓታት እንደሚወስድና ለ20 ታዳጊዎችም ሲከፋፈል ሦስት ሳምንታትን እንደሚፈጅ ሞያዊ አስተያየቱን ሰጥቷል።
አንዳንድ የአውሮፕላኑ ክፍሎችና ሞተሩ በሰለጠኑ ሰዎች የተገጠሙ ሲሆን አጠቃላይ አውሮፕላኑ የተገጣጠመው በታዳጊዎቹ ነው።
ታዳጊዎቹ በናሚቢያ ካረፉ በኋላ የመጨረሻ መዳረሻቸው ከሆነችው ግብፅ ከመድረሳቸው በፊት በዚምባብዌ፣ ማላዊ፣ ታንዛንያ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደሚያርፉ ተዘግቧል።












