የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት የቁንጅና ውድድር አሸናፊዋ በተፈጥሮ ፀጉሯ ልታጌጥ ይገባል ሲሉ ተቹ

የዩጋንዳ ቁንጅና ውድድር አሸናፊዋ ኩዊን አበንካዮ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የአፍሪካ ቆንጆ ተብላ የተሰየመችውን የዩጋንዳ ቁንጅና ተወዳዳሪ የህንድ ፀጉር ቀጥላለች በሚል ተቹ።

ኩዊን አበንካዮ ካሸነፈች በኋላም የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ፎቶዋን በትዊተር ገፃቸው ላይ አድርገው "የአፍሪካን ቁንጅና በተፈጥሯዊ መልኩ ልናሳይ ይገባል" ብለዋል።

ሙሴቪኒ "የህንድ ፀጉር" ሲሉ ምን ለማለት ነው ተብለው ሲጠየቁም ቃል አቀባዩ ዶን ዋንያማ "ፎቶውን ተመልከቱትና ምን ዓይነት ፀጉር እንደሆነ ማየት ትችላላችሁ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ጨምረውም "ተፈጥሯዊ ያልሆነ ዊግ ፀጉር ቀጥላለችና በተፈጥሮ ፀጉሯ ለምን አታጌጥም ነው ያሉት" ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ አበንካዮ ምርጫዋ ሊከበር ይገባል በሚል የደገፏት ሲሆን፤ የህንድ ፀጉር የሚለው የፕሬዚዳንቱ አባባል ከፍተኛ ውርጅብኝን አስተናግዷል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንድትሰጥ ቢቢሲ ጠይቋት ነበር። ከፕሬዚዳንቱ ጋር በአንድ ጉዳይ እንደምትስማማ ገልፃ " የምዕራቡ ዓለም የሚያደርገውን ነገር በሙል ኮፒ ልናደርግ አይገባም " ብላለች።

ነገር ግን ጨምራም " ለኔ ግን በጉዳዩ ላይ ያለኝ አስተያየት ግማሽ በግማሽ ነው። ስሜቴ እንደመራኝ ነው የማደርገው። በምንሰራው ስራም ሆነ ፀጉራችንን በምን መንገድ እንደምናስጌጥ የማንነታችን አካል መሆን የለበትም። እስከተመቸን ድረስ ማንኛውንም ነገር ልናደርግ ይገባል" ብላለች።

በማሸነፏም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ገልፃለች።

Presentational white space

የተወሰኑትም ጉዳዩን ወደ ትዊተር በመውሰድ በሴቶች ግላዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ የሚገባ ነው ብለውታል። የሴቶችን አካላዊም ሆነ በምን መንገድ ራሳቸውን ሊያቀርቡ እንደሚገባ ትዕዛዝ ሊሰጥ አይገባምም ብለዋል።

ምንም እንኳን ፕሬዚዳንቱን የደገፉ ቢኖሩም የፕሬዚዳንቱ ፀጉር አልባነትም ላይ አስተያየት የሰጡ አልታጡም።

Presentational white space

ምዕራባውያንን ማዕከል ያደረገ የቁንጅና እሳቤ

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ጥቁር የቁንጅና ተወዳዳሪዎች ምዕራባውያንን ማዕከል ያደረገ የቁንጅና እሳቤን (ዩሮሴንትሪክ) በከፍተኛ ሁኔታ እየተቹት ይገኛሉ።

የቆዳ ቀለማቸው ቀላ ያሉ ሴቶችና ፀጉራቸው ዘንፋላ (የተተኮሰ ፀጉር) እንደ ቆንጆ ውበት መለኪያ መታየቱ ስህተት ነው ብለዋል።

line