ቴህራን፣ አሜሪካ የሰላማዊ ዜጎች መጠቀሚያ የሆኑ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት አድርሳለች ስትል ከሰሰች

የፎቶው ባለመብት, SocialMedia
በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የሚካሄደው የሰላም ድርድሩ ከተቋረጠ ወዲህ የአሜሪካ ጦር በቅርቡ በፈፀመው የአየር ጥቃት የሲቪል መሠረተ ልማቶችን እየደበደበ ነው ስትል ቴህራን ከሰሰች።
የመንግሥት ሚዲያዎች እና የአካባቢ ባለሥልጣናት ድልድዮች፣ የባቡር ጣቢያ እና የአየር ማረፊያ መመታታቸውን ተናግረዋል። ቢቢሲ ቬሪፋይ በሆርሞዝጋን ግዛት በሚገኝ ድልድይ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል።
የአሜሪካማዕከላዊ ዕዝ (ሴንቲኮም) የዒላማዎቹንዝርዝር ባይገልጽም፣ ጥቃቶቹ "የኢራንን ወታደራዊ አቅም የበለጠ ለማዳከም" የታለሙ ናቸውብሏል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን የካቲት 21 2018 ዓ.ም. በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃቶች የተጀመረውን ጦርነት ለማስቆም ኢራን ወደ ድርድር እንድትመለስ ለማስገደድ ድልድዮችን እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን እንደሚመቱ ዝተው ነበር።
ኢራን የአሜሪካ ጦር ጥቃትን ተከትሎ በባህረ ሰላጤው ውስጥ በሚገኙ የዩኤስኤ ጦር ሰፈሮች እና አጋሮች ላይ የበቀል እርምጃ እንድትወስድ አድርጓታል።
አሜሪካ ለስድስት ተከታታይ ምሽቶች በኢራን ዒላማዎች ላይ የአየር ድብደባ ስትፈጽም ቆይታለች።
የኢራን የመንግሥት ሚዲያዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት ሐሙስ ምሽት ላይ በደቡብ ምሥራቅ ኢራን የሚገኘው የኢራንሻህር አውሮፕላን ማረፊያ፣ የባቡር ጣቢያ እና በሆርሞዝጋን ግዛት የሚገኙ ስድስት ድልድዮች ጥቃት እንደ ደረሰባቸው ዘግበዋል።
በሆርሞዝጋን የሚገኙ የክልል ባለሥልጣናት ደግሞ ሰባትሰዎች መገደላቸውን ይፋ አድርገዋል።
ቢቢሲ ቬሪፋይ እና ቢቢሲ ፐርሺያ በጋሪቭህ ድልድይ ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ቪዲዮን ትክክለኛለነት አረጋግጠዋል፤ በሌሊት የተቀረጹት ቪዲዮዎች በድልድዩ ላይ የእሳት ነበልባል ሲንቀለቀል አሳይተዋል።
በቀን የተቀረጹ ምስሎች በተሰበረው ድልድይ ዙሪያ የመንገድ ፍርስራሽ ያሳያል።
ሴንትኮም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ቢጠየቅም ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ የሚያክለው ምንም ነገር እንደሌለ ተናግሯል።
ትራምፕ በሚያዝያ ወር አሜሪካ በኢራን ድልድዮችንና የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን እንደምትደበድብ ከተናገሩ በኋላ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኃላፊ ቮልከር ቱርክ "ሆን ብሎ ሲቪሎችንና የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ማጥቃት የጦር ወንጀል ነው" ብለዋል።



















