የግብፅ መካነ መቃብር፡ ሳቃራ ፒራሚድ ኮምፕሌክስ አቅራቢያ አዲስ ግኝት ይፋ ተደርጓል

ከግብፅ፣ ካይሮ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳቃራ ኔክሮፖሊስ በተገኘው አዲስ መካነ መቃብር ጋዜጠኞች ሲገቡ ይታያል

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባለሙያዎች በጣም የተለየና ተጠብቆ የቆየ ያሉትን መካነ መቃብር ጋዜጠኞች ገብተው እንዲያዩ ተፈቅዶላቸው ነበር።

በግብፅ ቄሶች ያረፉበትና ላለፉት 4400 ዓመታት ተነክቶ የማያውቅ መካነ መቃብር ማግኘታቸውን አርኪዮሎጂስቶች አስታወቁ።

በግብፅ የአንቲኪዩቲስ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ የሆኑት ሙስጠፋ ዋዚሪ ባለፉት አስርት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ አስደናቂ ግኝት ነው ሲሉ ገልፀውታል።

በካይሮ አቅራቢያ ሳቃራ ፒራሚድ የተገኘው ይህ መካነ መቃብር በቀለማት ያሸበረቁ ሥዕላዊ መግለጫዎች፣ የፈርኦን ሐውልቶች እንዲሁም ዋህትይ የተባሉት የንጉሣዊ ቄስ ከእናታቸው፣ ከሚስታቸው እና ከዘመዶቻቸው ጋር በሚያሳይ ምስል የተሞላ ነው።

አርኪዮሎጂስቶች የመካነ መቃብሩ ባለቤት የመቃብር ክዳን ማግኘታቸውን ተከትሎ ሌሎች አዳዲስ ግኝቶችን ለመፈለግ በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 16 ቁፋሮ መጀመራቸው ታውቋል።

በሳቃራ መካነ መቃብር ውስጥ የሚገኘው በቀለም ያሸበረቁት ሥዕላዊ መግለጫዎች

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የግብፅ ፒራሚድ በሚገኝበት ሳቃራ ጥንታዊው ኔክሮፖሊስ ሰፊው መካነ መቃብር የተገኘበት ቦታ
የመካነ መቃብሩ ውጫዊ ክፍል የሚያሳየው በድንጋይ የተሰራውን ረዥም ግድግዳ

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የመካነ መቃብሩ ውጫዊ ክፍል የሚያሳየው በድንጋይ የተሰራውን ረዥም ግድግዳ
በወፎች ፣ በሰዎች ምስል ፣ በቅርፃ ቅርፆች ያጌጠው ግድግዳ

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በጥንታዊ የግብፅ ጽሁፍ እንዲሁም በሥዕላዊ መግለጫዎች የተሸፈነው መካነ መቃብር
በመካነ መቃብሩ ላይ የተሰሩ የአራት ሰዎች ሐውልት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በመካነ መቃብሩ ላይ የተሰሩ የሰዎች ሐውልት
ሙስጠፋ አብዶ አዲስ በተገኘው መካነ መቃብር ቆመው ይታያሉ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, የቁፋሮው ፕሮጀክት መሪ የሆኑት ሙስጠፋ አብዶ፤ መካነ መቃብሩ 10 ሜትር ርዝመት፣ 3ሜትር ስፋትና 3ሜትር ከፍታ አለው
በመካነ መቃብሩ ውስጥ የሚታየው ቀለም ያለው ሐውልት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በጥንታዊቷ ግብፅ ቄሶች ልዩ ክብር ይሰጣቸው ነበር
በቅርቡ በተገኘው መካነ መቃብር ያሉ ሥዕላዊ መግለጫዎችን አንድ ሰው ፎቶ ሲያነሳ የሚያሳይ ምሥል

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, የመካነ መቃብሩ ቀለም ላለፉት 4400 ዓመታት በጥሩ ሁኔታ ይገኛል
ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 2500 - 2350 ድረስ ግብፅን ሲመሩ የነበሩት ዋህቲይ ሐውልት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 2500 - 2350 ድረስ ግብፅን ሲመሩ የነበሩት ዋህቲይ ሐውልት
የመካነ መቃብሩ ባለቤትና ቤተሰቦቹ የሚያሳይ ባለ ቀለም ምስል

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, ዋናውን ቄስና ቤተሰቦቹን የሚያሳየው በቀለም ያጌጠው ግድግዳ
የአርኪኦሎጂስቱ ሰራተኛ በቄስ ዋህቲይ መካነ መቃብር ውስጥ ቆመው ይታያሉ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, አርኪዮሎጂስቶች መካነ መቃብሩ ላይ ተጨማሪ ምርምር ለማድረግ አቅደዋል።