በእስራኤሏ ከተማ ሲሳሪያ 900 ዓመታትን ያስቆጠሩ የወርቅ ሳንቲሞች ተገኙ

ዕቃው ተገኘው በጥንታዊው የእስራኤል የወደብ ከተማ ሲሰሪያ ነው

የፎቶው ባለመብት, Yaniv Berman

የወርቅ ሳንቲሞቹ ስብስብ በእስራኤል የጥንት ወደብ ከተማ ሲሳሪያ በአርኪዎሎጂስቶች ቁፋሮ ከ900 ዓመታት በኋላ የተገኘ ነው።

የወርቅ ሳንቲሞቹ ከአንድ የጆሮ ሎቲ ጋር በነሐስ ማሰሮ በድንጋዮች መካከል የተገኙ ሲሆን በቁጥር 24 ናቸው። ምን አልባትም አንድ ቀን አውጥቼ እጠቀምበታለሁ በሚል በአንድ ግለሰብ የተቀበሩ ሳይሆኑ እንዳልቀረና ሳይጠቀሙበት እንደቀሩ ተነግሯል።

የሳንቲሞቹ ባለቤት በአውሮፓውያኑ 1101 በነበረው የጅምላ ጭፍጨፋ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ አርኪኦሎጂስቶቹ ያስረዳሉ።

እንዚህ ሳንቲሞች በሲሰሪያ የዓለም ቅርስ ጥበቃ ለመስራት በተደረገ ቁፋሮ ወቅት የተከሰቱ ሲሆን በሁለት ድንጋዮች መካከል ተቀብረው ነው የተገኙት።

ይህም በሲሰሪያል አስገራሚ ታሪክ የመስቀል ጦርነት በድል ለመጠናቀቁ ግኝቱ አንዱ ማሳያ እንደሆነ የእስራኤል የጥንት ቅርሶች ጥበቃ ባለስልጣናት አስረድተዋል።

ባለስልጣናቶቹ የተፃፉ መረጃዎችን ጠቅሰው በአውሮፓውያኑ ከ1100 እስከ 1118 ባሉት ዓመታት አብዛኞቹ የሲሰሪያ ነዋሪዎች በእየሩሳሌም የመስቀል ጦርነት መሪ በባልድዊን መጀመሪያ ተገድለዋል።

በመሆኑም "የእቃዎቹ ባለቤት እና ቤተሰቦቹ በዘር ጭፍጨፋው እንደተገደሉ አሊያም በባሪያ ንግድ እንደተሸጡና ወርቁን ማውጣት እንዳልቻሉ በምክንያታዊነት ማሰብ ይቻላል" ይላሉ የቁፋሮው ዳሬክተሮች ዶክተር ፒተር ግንደልማን እና ሞሃመድ ሃታር።

የቅርብ ግኝት እንደሚያስረዳው በሁለት ተቀራራቢ ቦታዎች ሌሎች ሐብቶችም ተገኝተዋል። አንደኛው የወርቅ ማሰሮና የብር ጌጣጌጦች ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1960 የተገኘ ነው ሁለተኛው ደግሞ በ1990 የተገኘው የነሐስ ዕቃ ነው።

እነዚህ ግኝቶች በቅርቡ በእየሩሳሌም በሚገኘው የእስራኤል ሙዚየም ውስጥ ተጠብቀው ይገኛሉ።

በአውሮፓውያኑ 2015 እንዲሁ በእስራኤል ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ጠላቂዎች ረጂም እድሜ ያስቆጠሩ የወርቅ ሳንቲሞች ቁርጥራጮችን አግኝተዋል።

ሳንቲሞቹ በቁጥር 2000 ሲሆኑ ከ1000 ዓመት በላይ አስቆጥረዋል፤ በባህር ጠላቂ ቡድኖች ተቀብረው የቆዩ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።