የሳዑዲው ጋዜጠኛ ለመገደሉ ቱርክ አሳማኝ ማስረጃ እንድታቀርብ አሜሪካ ጠየቀች

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ተራምፕ

አሜሪካ የጠየቀችው ሳዑዲው ጋዜጠኛ ጀማል ጋሾጊ በርግጥም በኢስታንቡል የሳውዲ ቁንስላ ውስጥ መገደሉን የሚያሳይና የሚያሳምን የተቀረፀ ማስረጃ እንድታቀርብላት ነው።

ትናንት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የተቀረፀ የዚህ ዓይነት ማስረጃ ካለ ጠይቀናል" ሲሉ በዋይት ሃውስ ላጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ሳዑዲው ጋዜጠኛ ካሾጊ ከ 16 ቀን በፊት በኢስታንቡል ከሚገኘው የአገሩ ማለትም የሳውዲአረብያ ቁንስላ ከሚገኝበት ህንፃ ከገባ በኋላ ማንም አላየውም።

ጋዜጠኛው ከመጥፋቱ በፊት የፃፈውን ፅሁፍ ዋሽንግተን ፖስት አትሞት ነበር።በፅሁፉ በመካከለኛው ምስራቅ የሚዲያ ነፃነት እንደሚያስፈልግ የሚገልፅ ነው።

የጋዜጣው ኤዲተር ካረን አቲሃ ካሾጊ በደህና ይመለሳል በሚል የፅሁፉ ህትመት እንዲዘገይ ተደርጎ እንደነበር ተናግራለች።

"አሁን ግን ያ እንደማይሆን እያመንኩ ነው።አሁን ግን ፅሁፉ የካሾጊ የመጨረሻ ፅሁፍ እንደሆነ አውቄአለው።

"ፅሁፉ ካሾጊ በአረቡ አለም የሚዲያ ነፃነት እንዲኖር ፅኑ ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ ነው። ህይወቱንም የሰጠው ለዚሁ ነው"ብላለች።

ሳዑዲ አረብያ ከአሜሪካ ጥብቅ ግንኙነት ካላቸው አገራት አንዷ በመሆኗ የካሶጊ የደረሰበት አለመታወቅ አሜሪካን ከባድ ሁኔታ ውስጥ ከትቷታል።