ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የደምህት ወታደሮች የመኪና አደጋ ደረሰባቸው
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደምህት) ወታደሮች ዛሬ ጠዋት ከኤርትራ ወደ ዛላምበሳ በሚመጡበት ወቅት ነበር ሰገነይቲ በሚባለው የኤርትራ ድንበር ውስጥ የመኪና አደጋ ያጋጠማቸው።
በአደጋው ብዙ የደምህት ወታደሮች እንደተጎዱ ከአካባቢው ወደ ዛላምበሳ የመጣ የድርጅቱ አመራር አባል ለቢቢሲ ተናግሯል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የወታደሮች ቁጥር በውል ባይገልጽም፤ ሰራዊቶቹን የያዘች መኪና እንደተገለበጠች ግን አረጋግጧል።
መንግሥት ባቀረበው የሰላም ጥሪ መሰረት ከ2000 በላይ የደምህት ወታደሮች ዛሬ ማለዳ ዛላምበሳ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሠራዊቱን አባላት የሚቀበሉ የህዝብ አውቶብሶችም በዛላምበሳ ከተማ ተዘጋጅተዋል።