ዛምቢያ ህገወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አዋለች

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የጦር ማሳሪያዎችን ይዘው ነበር
የምስሉ መግለጫ, ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የጦር ማሳሪያዎችን ይዘው ነበር

ዛምቢያ ህገ ወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ አግኝቻቸዋለሁ ያለቻቸውን ሁለት ቻይናውያንን አሰረች።

የአገሪቱ ፖሊስ እንዳስታወቀው ሁለቱ የቻይና ዜጎች ለእስር የተዳረጉት ለአካባቢው የፀጥታ ሃይል አባላት ህገወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ በመያዛቸው እንደሆነ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአገሪቱ ጎብኝዎች በብዛት በሚገኙበት ሊቪንግስተን ከተማ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህንን ተግባር በማቀነባበር ወንጀል ተጠርጥረው የዛምቢያ ዜጎችን ጨምሮ እስካሁን 11 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ አስታወቋል።

የአገሪቱ ደቡባዊ ግዛት ፖሊስ ኮሚሽነር ቦኒ ካፔሶ እንዳስታወቁት የዛምቢያ ሊቪንግስተን ከተማ የደህንነት ኃላፊ በድርጊቱ እጃቸው አለበት ተብሎ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ጠመንጃ፣ የእጅ ሽጉጦችንና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን መያዙንም ፖሊስ ጨምሮ ተናግሯል።

የደህንነት ተቋሙና ተጠርጣሪዎቹ የቀረበባቸው ክስ ላይ ያሉት ነገር እንደሌለም ተገልጿል።