ፍየሎችም «ከፍትፍቱ ፊቱ» ይሉ ይሆን?

የፎቶው ባለመብት, Andia
ፍየሎች በተለይ ደስተኛ ገፅ ያለው የሰው ፊት ቀልባቸውን እንደሚገዛው በጥናቱ ተጠቁሟል።
የመርማሪዎች ቡድን ጥናቱን ለማካሄድ ከተጠቀመባቸው መንገዶች አንዱ የተለያዩ ስሜቶችን የሚያሳይ የአንድ ሰው የፊት ፎቶ በ1.3 ሜትር ርቀት አራርቆ በመስቀል ለፍየሎች ማሳየት ነው።
ፍየሎችም ከሌሎች በተለየ ፈገግታ እና ደስታን በሚያሳየው ፎቶ ዙሪያ እንደተኮለኮሉ ተነግሯል።
በደስተኛው ገፅ ከመሳብ በተጨማሪ ከሌሎች ፎቶዎች በተለየ ከፍ ላለ ጊዜ እንዳጤኑት ተመስክሯል።
ከጥናቱ አድራጊዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር አለን ማክኤልጋት ጥናቱ የሰው ልጅ የቅርብ ወዳጆች ከሆኑት ውሾች እና ፈረሶች በተጨማሪ ሌሎች እንስሳትም የሰውን ስሜት የማንበብ አቅም እንዳላቸው ፍንጭ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።












