ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

የፎቶው ባለመብት, Anadolu Agency
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሰታውቋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን ቀደም ሲል በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አምባሳደር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ ሚንስትር እንዲሁም የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር በመሆን አገልግለዋል።
ኢትዮጵያ በአሥመራ በቅርቡ ኤምባሲዋን አንደምትከፍትም ተነግሯል።
ከቀናት በፊት ኤርትራ በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን ብትከፍትም አምባሳደር ግን እስካሁን አልተሾመችም።
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኤርትራ ጋር ያለኝን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አጠናክሬ እሰራለው ብሎዋል።















