የፕሮፌሰሩ ዳንስ ሕንዶችን አስደንቋል

ህንዳዊው ፕሮፌሰር ከባለቤታቸው ጎን አስደናቂ ትርዒት በማሳየት ላይ ሳሉ

የፎቶው ባለመብት, YOUTUBE/SANJEEV SRIVASTAV

ሰውዬው በከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተከበሩ የኤሌክትሮኒክስ ፕሮፌሰር ናቸው።

በአጋጣሚ ነው ነገሩ የተከሰተው።

በተጠሩበት ሠርግ ድንገት ነሸጥ አድርጓቸው ወደ መድረክ ከወጡ በኋላ ባሳዩት ልዩ የዳንስ እንቅስቃሴ ታዳሚውን አስደምመዋል።

"እንዴት አንድ ከጸጉራቸው ገባ፣ ከሆዳቸው ገፋ ያሉ ፕሮፌሰር በዚህ ዓይነት ቅልጥፍና ሊደንሱ ይችላሉ?" የሚለው ሕንዳዊያንን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን እያነጋገረ ይገኛል።

በፍጹም በዚህ ቅጽበት እንዲህ ዝነኛ እሆናለሁ አላልኩም ብለዋል ፕሮፌሰሩ ለጋዜጠኞች።

የእርሳቸው ቪዲዮ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በፍጥነት መዘዋወሩን ተከትሎ እጅግ ዝነኛ ሕንዳዊ ሙዚቀኞችና አርቲስቶች ሳይቀሩ ፕሮፌሰሩን ለማድነቅ ወደ ትዊተር ገጻቸው አቅንተዋል።

የፕሮፌሰሩ ትዊተር ገጽ በአጭር ጊዜ 3ሺህ ተከታዮችን አግኝቷል።

በሕንድ ትዊተር ገጾች #ዳንሰኛው-አጎቴ ወይም #dancinguncle በሚል "ሀሽታግ" ተጥለቅልቀው ውለዋል።

"ባለፉት ቀናት እንቅልፌን መተኛት እንኳን አልቻልኩም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ ዝና እረፍት እንደነሳቸው ሲያብራሩ።