ከረመዳን ጾም ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ እሳቤዎች

ፆም

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በረመዳን የጾም ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ ሁሉም የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች፤ ፀሐይ ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ከማንኛውም አይነት ምግብ እና መጠጥ ይቆጠባሉ።

የጾሙ ዋና አላማ መንፈሳዊነትን መጨመር እና ሐይማኖታዊ ክብርን ማሳየት ሲሆን፤ ረጅም ጸሎቶችን በማድረግ እና ራስን በመቆጣጠር የሐይማኖቱ ተከታዮች የጾሙን ወቅት ያሳልፋሉ።

ምንም እንኳ ይህን ማድረግ ቀላል መስሎ ቢታይም፤ የብዙ ሰዎችን አስተሳሰብ መከፋፈል የቻሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች እና አፈ ታሪኮች አሉ።

ሙሉውን ቁርአን በቃሉ የሚያስታውሰው ሻቢር ሃሳን የእስላማዊ ሳይንስ እና ሸሪዓ ሕግ ተማሪ ነው። በረመዳን ጾም ወቅት በተለምዶ የምንሰራቸውን ስህተቶች እንዲህ ያስቃኘናል።

'ጥርስ መፋቅ'

እንደ ዘርፉ ምሁራን ከሆነ ጥርስን መፋቅ ጾሙን መግደፍ ማለት አይደለም። አንዳንድ ሰዎች ጥርሳቸውን በሚፍቁበት ወቅት ወደ አፋቸው የሚገባው የጥርስ ሳሙና ጣእም ጾማቸውን እንዳስገድፍባቸው ይሰጋሉ።

ነገር ግን ይህ ተቀባይነት የለውም ቢሉም ምሁራኑ፤ ለጥንቃቄ የሚረዱ አንዳንድ መፍትሄዎች አሉ ይላል ሃሳን።

የመጀመሪያው ትንሽ የጥርስ ሳሙና መጠቀም ሲሆን፤ ቀለል ያለ ጣዕም ያላቸው ምርቶችን መጠቀምም እንደሚረዳ ይመክራል።

በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅትን እውቅና ያገኙ ከተፈጥሮአዊ ተክሎች የሚሰሩ የጥርስ ሳሙናዎችን መጠቀምን ደግሞ ተጨማሪ አማራጭ ነው።

የጥርስ መፋቂያ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

'ምራቅ መዋጥ'

የራስን ምራቅ መዋጥ ምንም ችግር የለውም፤ እንደውም ይበረታታል።

"ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ምንም መሰረት የለውም" ይላል ሃሳን። "ምራቅን መዋጥ ተፈጥሮአዊ ሂደት ነው። ስለዚህ ጾምን አያስገገድፍም።''

ጾሙን ሊያስገድፍ ሚችለው ግን የሌላን ሰው ማንኛውም አይነት ፈሳሽ ወደ ውስጥ ማስገባት ነው።

የሌላ ሰውን ምራቅ ወደ ውስጥ ማስገባት በጾም ወቅት እጅግ ክልክል እና ሀጢያት ነው፤ ይላል የእስላማዊ ሳይንስ እና ሸሪዓ ህግ ተማሪው ሃሳን።

"ከዚህ ጋር ተያይዞ የፍቅር ጓደኛም ሆነ የትዳር አጋርን መሳም አይፈደቀድም'' የሚለው ሃሳን፤ በዚህ ቅዱስ ወቅት ራስን ከእንደዚህ አይነት ስሜቶች መቆጣጠር እና ከምግብ እና ውሃ መራቅ ወደ አምላክ ያቀርባል ሲል ያክላል።

በጾሙ ወቅት ከምግብ እና ውሃ ብቻ ሳይሆን፤ ከሃጥያት፣ ከክፉ ሃሳብ እና ሌሎችን ከማስቀየም መቆጠብ አለባቸው ሲል ሃሳን ያክላል።

'በስህተት መመገብ ወይም መጠጣት'

"ጾም ላይ መሆኖን ረስተው በፍጹም ስህተት ከተመገቡ ወይም ውሃ ከጠጡ ጾሞን እንዳፈረሱ አይቆጠርም። ነገር ግን ባስታወሱባት ቅፅበት መመገብንም ሆነ መጠጣትን ማቆምዎን አይዘንጉ" ይላል ሃሳን።

"ሰውነትዎን በሚታጠቡ ወቅት ግን ውሃ ወደ ሰውነትዎ ቢገባ ጾሙ እንደፈረሰ ይቆጠራል።''

እንደ ሃሳን ከሆነ ሐይማኖታዊ በሆነ መንገድ ሰውነታችንን በምናጸዳበት ጊዜ ውሃ ወደ አፋችን እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ሲል ይመክራል።

መድሃኒት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

'መድኒት መውሰድ'

የእንግሊዝ እስላማዊ ምክር ቤት እና ዓለም አቀፉ የግላኮማ ማኅበር በረመዳን ጾም ወቅት እንደ አይን ጠብታ እና ክትባት ያሉ ጥቂት መድኃኒቶችን መጠቀም እንደሚቻል ያስቀምጣሉ።

ነገር ግን የሚዋጡ መድኃኒቶችን ከጾም በፊተ አልያም በኋላ መወሰድ እንዳአለባቸው ይመከራል።

እንደ ሃሳን ሃሳብ ከሆነ ህክምና ላይ ያለ ሰው በመጀመሪያ ጾሙን መጾም አለብኝ ውይ? ብሎ መጠየቅ አለበት።

'የጾም ግዴታ'

በእስልምና ሐይማኖት ማንኛውም ከ15 ዓመት በላይ የሆነ ጤናማ ሰው ይህን ዓመታዊ ጾም መጾም ግዴታ ነው።

ይሄ ማለት ህጻናት፣ ህመምተኞች፣ የአእምሮ ህሙማን፣ መንገደኞች፣ እርጉዞች እና የሚያጠቡ እናቶች የመጾም ግዴታ የለባቸውም።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ከህመሞ እንደሚድኑ እርግጠኛ ከሆኑ ግን ጾሙን መጀመር ይቻላል ሲል ሃሳን ይናገራል።

ከባድ ህመም ላይ ያሉ በሽተኞች ግን ካገገሙ በኋላ መጾም እንደሚችሉና አቅመ ደካማ ቤተሰቦችን በመመገብ ፊድያህ ተብሎ የሚጠራውን ሥርዓት መፈጸም እንደሚችሉ ሃሳን ጨምሮ ይገልፃል።