‘ቤቴን ከ28 ስደተኞች ጋር እጋራለሁ’

Frank Okoro sits on a chair in a red t-shirt

የፎቶው ባለመብት, BBC

የምስሉ መግለጫ, ፍራንክ ኦኮሮ ደሞዙን ቤተሰቡንና 28 ስደተኞችን ለማስተዳደር ያውለዋል

የናይጄሪያ የአደጋ ጊዜ ሃላፊዎች እንደሚሉት ካለፈው ጥቅምት ወዲህ ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ሃገሪቱን ከካሜሮን ጋር በሚያዋስናት ድነበር በኩል መግባታቸው ሲገልጹ ይህ ቁጥርም እያደገ ነው ብለዋል።

ስደተኞቹ በደቡባዊ ሃገሪቱ ክፍል ተገንጣዮች የራሳቸውን ግዛት "የአምባዞኒያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ" ብለው መመስረታቸውን ተከትሎ ደም አፋሳሽ ዘመቻ በቶሩ ስለተከፈተባቸው ነው።

በደቡባዊ ናይጄሪያ በምትገነው አግቦኪም ቢቢሲ 28 ስደተኞችን በቤቱ ያስጠጋውን እና የአራት ልጆች አባት የሆነውን ፍራንክ ኦኮሮን አግኝቶታል።

የ57 ዓመቱ ፍራንክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር እና እምነቱም ጠንካራ ነው።

ደሞዙን እና ከካካዋ እና ከከሳቫ እርሻ የሚያገኘውን ገቢም ብዛት ያላቸውን እንግዶቹን ለማስተናገድ እየተጠቀመበት ነው። አንዳንዶቹ ካሜሮናዊት ሆነችው የሚስቱ ዘመዶች ሲሆኑ ሌሎች ግን ምንም ግንኙነት የላቸውም።

በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆናቸው ነው አብረውት እንዲሆኑ የፈቀደው። ለሁሉም የሚበቃ ማረፊያ ቦታ ማዘጋጀት ግን አዳጋች ነው።

"መሬት ላይ ምንጣፍ እንዘረጋላቸዋለን" ይላል። "ሁሉም ህጻናት መሬት ይተናሉ ወይም ደግሞ እናቶቻቸው አቅፈዋቸው በሰላም ተኝተው ጠዋት እንዲነቁ ነው የምፈልገው።"

እንግዶቹ የሚሰራውን የትኛውም ሥራ ያግዙታል። ይህ ማለት "በመርህ ደረጃ የማይሰሩ አይበሉም" ማለት ነው።

A group picture of displaced women and children together in a village
የምስሉ መግለጫ, አብዛኛዎቹ ስደተኞች ሴቶች እና ህጻናት ናቸው

እንደገበሬ ብዙ የሚሰሩ ሥራዎች አሉ። "አምላክ በትልቁ እየረዳን ነው" ይላል ፍራንክ። "የቤቱ አባወራ እንደመሆኔ ሁኔታውን ለመቋቋም እኔ ብዙ መጣር ይኖርብኛል" ሲል ያምናል።

የሰፊው ቤተሰብ ወይንም የሌሎች ደግ አሳቢዎች ድጋፍ ባይኖር ኖሮ ስደተኞቹ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋጥማቸው ነበር። ከአካባቢውም ሆነ ከዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ የሚያገኙት አንዳንዴ ነው። መሠረታዊ የጤና አገልግሎትም አያገኙም። ልጆቻቸውም የትምህር ዕድል አያገኙም።

ከዚህ ውጭ ያላቸው አማራጭ ግን ወታደራዊ ትቃት በሚፈጸምባት ካሜሮን መቆየት ነው መሆኑን ይገልጻሉ።

'በቁጥቋጦ ውስጥ ለስምንት ቀናት ተጉዣለሁ'

ወጣት የሆነው አባት ሬኔ ወታደሮች መንደራቸውን ሙሉ በሙሉ አጥፍተው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ከባለቤቱና ከልጆቹ ጋር መለያቱን ለቢቢሲ አስታውቋል።

ምስጋና ለአንድ ሞተረኛ ቅን ሰው ይሆንና የሚወዳቸው ሰዎች ከረዥም ጉዞ በኋላ ወደ የናይጄሪያ ድንበርን አልፈው መግባት ችለዋል። እሱ ግን ግጭቱን ለማምለጥ ከሳምንት በላይ በቁጥቋጦ ውስጥ ለመጓዝ ተገዷል። በዚህ ወቅትም ህይወቱን ለማቆት ከቻካ ውስጥ ፍራፍሬ በመልቀም እና የወንዝ ውሃ ለመጠታት ተገዷል።

ለሁለት ቀናትም በየቦታው ሲማስን ቆይቶ ነው እግረኛ መንገድ ያገኝው። መንገዱ በናይጄሪያዋ ክሮስ ሪቨር ግዛት ወደምትገኘው ባሱ መንደር የወሰደችው ሲሆን ዕድለኛ ሆኖም ቤተሰቦቹን አግኝቷል።

Rene, 32, pictured in a village in Nigeria's New Cross State
የምስሉ መግለጫ, ሬኔ ለሳምንት ያህል ቁጥቋጦ ውስጥ ሲጓዝ ቆይቷል

አሁን ከካሜሮን 27 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው ኢኮም ከተማ ነው ተጠልለው የሚገኙት።

"በምንደራችን በሠላም ነበር የምንኖረው። በድንገት ወታደሮች ማህበረሰባችንን ወረሩት። በደቂቃዎች ውስት ጥይት ተኩስ ድምጽ ሰማን። ወደ ግራ ወደ ቀኝ መሮጥ ጀመርን። ለስምነት ቀናት በደን ውስጥ ሮጫለሁ።"

እንደ 32 ዓመቱ ሰው ከሆነ ይህ ህይወቱ መጥፎ ልምድ ነው። በደን እና በተራራ ላይ ሲጓዝ እግር ላይ ደረሰውን ጉዳት የሚያሳየውን ቁስል አሳይቶኛል።

A close-up picture of Rene's wounded foot, which is heavily scabbed
የምስሉ መግለጫ, ሬኔ በስደት ጉዞው ወቅት እግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበታል

እንደ ብዙ ስደተኞች በማህበረሰቡ አካባቢ ሠላም እሰኪሰፍን ድረስ ወደ ካሜሮን መመለስ አይፈልግም።

'ራቁቴን ወደ ወንዝ ወረወሩኝ'

የተሰደዱት ሴቶች በካሜሮን ጦር ጥቃት እንደደረሰባቸው ይገልጻሉ።

በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የምትገኘውንጉማ እሷና ሌሎች ሴቶች በካሜሮን ጦር "ተደብድበው፣ ራቁታቸውን ወደ ወንዝ ውስጥ ተወርውረዋል።" ሌሎች ስደተኞችን ጨምሮ እነሱም ወደ ናይጄሪያ መግባት የቻሉት በጀልባ ነው።

Nguma sits in a chair, whittling something with a knife
የምስሉ መግለጫ, ንጉማ ወታደሮች እንደደበደቧት ተናግራለች

ሬጂና ደግሞ ግጭት በተቀሰቀሰበት ወቅት ወደ ቤቷ ሮጣ በመሄድ ልጆቿን ልታድን ስትሞክር በሶስት ወታደሮች እንድትቆም ተደርጋለች።

ወደ ቤቷ ስትደርስ በወታደሮች መያዟን ገልጻለች። "ባልህ ያልሆነ ሰው ጡትህን ሲይዝህ፤ ወደራሱ አጥብቆ ሲይዝህ... ወታደሮች ድፍራሉ ሲባል ስለሰማሁ መጮህ ጀመርኩ።"

"ልጆቼ እየሮጡ ሲመቱ የጦሩ ባልደረባ አይቷቸው ቤቴ ኮሪደር ላይ ለቀቀኝ።"

ብዙዎቹ ወደ ናይጄሪያ የሸሹ ስደተኞች በተቀሰቀሰው ግጭት ያዩት ነገር አሁንም ጭንቀት እንደሚፈጥርባቸው ይገልጻሉ።

"ነጻነታችን ከታወጀ ወደ መንደሬ እመለሳለሁ" ትላለች ረጂና። "ጦርነቱ የማያበቃ ከሆነ ግን አልመለስም። ምክንያቱም ወታደሮቹን እፈራለሁ። እነዛ ትልልቅ የጦር መሣሪያዎች ልቤ ውስጥ ህመም አኑረዋል።"

"የመሣሪያ ተኩስ ድምጽ ስሰማ የሞትኩ ያህል ልቤ ወደ ውስጥ ትገባለች። እነዛ መሣሪያዎች እያሉ ካሜሮን ውስጥ መኖር አልፈልግም።"

Regina crosses her arms in front of her, flanked on either side by young children
የምስሉ መግለጫ, ሬጂና ቶርነቱ ካልቆመመ ወደ ካሜሮን እንደማትመለስ አስታውቃለች

በስደተኞቹ መካከል ስለ ካሜሮን እና ስለተሰደዱባት ናይጄሪያ ትልቅ ጥርጣሬ አለ።

በካሜሮን በኩል ባለወ የጦሩ ጥቃት ምክንያት ስደተኞች አሁን ወደ ናይጄሪያ ለመሻገር ያላቸው መንገድ ጠባብ ነው። ህጋዊዎቹ መንገዶች የሚቻሉ አይደሉም። ስለዚህ ድንበሩን ለማቋረጥ ግዴት ሚሆንባቸው ሰዎች በቁጥቋጦ ውስጥ መጓዝ ብቸና አማራጫ\ቸው ነው።

ግጭቱ በምን ምክንያት ነው?

አብዛኛው ህዝብ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ በሆነባት ካሜሮን አነስተኛ ቁጥር ያላቸው እንግሊዘኛ ተናጋሪ ካሜሮን አካባቢ ነዋሪዎች እንደተገለሉ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ይገልጻሉ።

በአውሮፓዊያኑ 2016 በተወሰኑ እንግሊዘኛ ተናጋሪ አካባቢዎች ከወና ወና መንግስታዊ ስራዎች ተገለናል፤ ፈረንሳይ ቋንቋ እና ፍትህ ዘዴ ተጭኖብናል በሚል ላይ ተቃውሞ ተጀመረ።

መንግሥት ለዚህ ምላሽ የሰጠው ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ነው። ከዚህ ባለፈ በእንግሊዘኛ ተናጋሪ አካባቢዎች ለረዥም ወራት ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ሆኖም ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን አንዳንዶች ነጻነት ታውጆ "የአምባዞኒያ ፌደራል ሪፐብሊክ" በእንግሊዘኛ ተናጋሪ የሰሜን ምእራብ እና ደቡብ ምዕራብ አካቢዎች እንዲመሠረት ጠየቁ።

አንዳንዶች የትጥቅ ትግል የጀመሩ ሲሆን ብዙ ቁጥር ያላቸው ጸጥታ አባላትም ተገደሉ።

መንግሥት ሰብዓዊ መብት አያያዝ ጥሰት መኖሩን ያስተባብላል። ጦሩ የሃገሪቱን ሉዓላዊ አንድነት ብቻ እየጠበቀ ነው ይላል።

መንግሥት በየትኛውም ቅሬታ ዙሪያ ለመነጋገር በሩ ክፍት ቢሆንም የትኛውንም የመገንጠል ወይም የአመጽ ተግባር እንደማይቀበል ካሜሮን መንግሥት ቃል አቀባይ ኢሳ ቺሮማ ባካሪ አስታውቀዋል።

ናይጄሪያ በሰሜናዊ ሃገሪቱ ክፍል በኮ ሃራምን ጥቃትን የሸሹ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን ጉዳይ በመፍታት ላይ እያለች ካሜሮን ስደተኞች መጨመር ችግሩን አባብሶታል።

John Inaku
የምስሉ መግለጫ, ጆን ኢናኩ-በክሮስ ሪቨር ግዛት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኃላፊ

አብዛኛዎቹ በደቡባዊ ክሮስ ሪቨር ግዛት እና ማዐከላዊ ቤኑ ግዛት ነው የሚገኙት።

"እስካሁን ያለው ልምድ አስቸጋሪ ሲሆን ሰዎች ቁጥር መጨመሩም በጣም የሚያሳዝን ነው። በተለይ ደግሞ በጀቱ ያላካተታቸው ሰዎች ሲሆኑ የከፋ ይሆናል። አይደለም ለመመገብ ለማሰባበሰብም አስቸጋሪ ነው" ሲሉ በክሮስ ሪቨር ግዛት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኃላፊ ጆን ኢናኩ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ስደተኞቹን ለመርዳት ከሚሞክሩት መካከል ይጠቀሳሉ።

የካሜሮን ስደተኞችን በጉልበት ከናይጄሪያ ለመመለስ የሚደረግ ጥረት ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ በመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስጠንቅቋል።

እንግለዘኛ ተናጋሪዎች ባለቡት ካሜሮን ክፍል ያለው ውጥረት አሁንም ከፍተኛ ሲሆን በናይጄሪያ ያሉ ስደተኞች ምን ኣህል እንደሚቆኡ አልታወቀም።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቋሚ መጠለያ በየጊዜው እየጨመረ ለሚገኙት ስደተኞች ለማቋቋም ለማስራት እያሰቡ መሁን እየገለጹ ነው። እንደጀራተኞቹ ከሆነ ሠላም የማይመጣ ከሆኑ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት የስደተኞች ቁጥር ከሚሊዮን ሊበልጥ ይችላል።

እንደዚህ ከሆነ ደግሞ በፍራንክ ቤት በእንግድነት የተገኙት ሰዎች ላልተወሰነ ጊዜ በዛው ሊቆዩ ነው።