"በሜዴትራንያን ባህር ልሰምጥ ነበር"

የፎቶው ባለመብት, ነሽነሽ
ሽሻይ ተስፋአለም እባላለሁኝ። ነሽነሽ ደግሞ ቅጥያየ ነው። የኤርትራዋ ኣስመራ ከተማ ተወልጄ ያደግኩባት ከተማ ናት።
ሳዋ ስለጠና ከወሰድኩኝ ኋላ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኣስተማሪ ነበርኩኝ። በተጨማሪ ሙዚቃ እና ቀልድ እሰራ ነበር።
አስተማሪ ሁኜ የማገኘው ደሞዝ ስለማይበቃኝ ከቤተሰቦቼ ተጨማሪ ብር እለምን ነበር።
የኤርትራ ነባራዊ ሁኔታ አገር ውስጥ ለመኖር አልተመቸኝም። እናም ከአገር ለመውጥት ወሰንኩኝ። ከ 2 አመት በፊት እግሮቼ ለስደት ተነሱ።
እናም ከከባድ የእግር ጉዞ በኋላ በድንበር ወደ ኢትዮጵያ ገባሁኝ። በኢትዮጵያ ዓዲሓርሽ በሚባል የስደተኞች ካምፕ ለሰባት ውራት ቆየሁኝ።
በስደተኞች ካምፕ ብኖርም ካምፑ ለኔ ጥሩ ነበር። ትግራይ ውስጥ በሽረ ከተማ ከሚገኝ የባህል ቡድን በመሆን ለህዝብ ሙዚቃ በማቅረብ፡ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ ፍቅርና ሰላም እንቀሰቅስበት ነበር።
በዓዲሓርሽ ስደተኞች ካምፕ በነበርኩበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን አስተማሪዎች በሞያ ይረዱን ስለ ነበር፡አንዳንድ ዘፈኖች ሰርቼ ነበር።
የኢትዮጵኣ ህዝብ ስታዘብ በጣም እቀና ነበር። ከካመፑ ወጥቼ ስንቀሳቀስ፡ ህዝቡ ማን ነህ የሚለው የለም፡ በነፃነት ይንቀሳቀሳል።
ኣኔ የኔው ኤርትራዊ ህዝብ እንዲህ አይነት ነፃነት ቢያገኝ ምን አይነት እፎይታ ማግኘት በቻለ ብየ እቀናለው።
እንዲሁ በስደተኞች ካምፕ እኖራለው እንጂ፡ በስደተኞች ካምፕ እንደምኖር አይሰማኝም ነበር። አስተማሪዎቹ ገንዘብ እየከፈሉ ያስተምሩን ነበር።

የፎቶው ባለመብት, ነሽነሽ
በስደተኞች ካምፕ ሁሌ እየተጦርኩኝ መኖሩን አልመረጥኩትም። እናም ለተሻለ ሂወት ዳግመኛ ወደ ስደት ተነሳሁኝ፡ ኣውሮፓ ለመግባት።
ከጓደኞቼ ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ወደ ሲዳን፡ ከዛም ሰሃራ በረሃ በማቋረጥ ከባድ ዕግር ጉዞ በኋላ ሊቢያ ገባሁኝ። በጣም ከባድ ጉዞ ነበር።
ሊቢያ ከገባን በኋላም ከባድ የፈተና ናዳ ይወርድብን ጀመር። ለሶስት ወራት ያክል በደላሎች ተደበደብን። ሁሌ ገንዘብ እንደተጠየቅን ነው።
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለደላሎች ረብጣ ሺዎች በመክፈል በሶስት ጀልቦች ተከፋፍለን፡ ወደ ጣልያን በሜድትራንያን ባህር ጉዞ ጀመርን።
እኛ ጋር ከነበሩ አንደኛዋ ጀልባ ጣልያን ገባች።
እኛ ግን እፎይ ሳንል በሄድንበት ፈተና ይከተለን ጀመር።
ሁለተኛዋ ጀልባ አይናችንን እያየን ከባህሩ መሃል ሰመጠች። የ 500 ኤርትራውያን ስደተኞች ህልምና ሂወት እንደ ውሃ ተነነ፡ ሁሉኑም የባህር ዓሳ ሲሳይ ሆኑ።

የፎቶው ባለመብት, ANGELOS TZORTZINIS
ዳግማይ ስደት
እኛው የያዘችው ጀልባም አንድ ሰዓት ከተጓዝን በኋላ ጭር ባለው ባህር ቆመች።
ምንም መንቀሳቀስ አልቻለችም። በአ ንደኛው ጭንቅ ሌላ ጭንቅ አጋጠመን፡ አሁን ሁላችነም ተስፋ ቆረጥን።
አትጥፉ ሲለን የሊቢያ የባህር ወደብ ጠባቂዎች ደርሰውብን ወደ ሊቢያ መለሱን።
ይህ ሁሉ ሁኖም አሁንም ተስፋ አልቆረጥንም። እንደ አዲስ ለደላሎች ብር ከፍለን ወደ የምናስባት ጣልያን ገባን።
ጣልያን አገርም ሌላ የስደጠኞች ካምፕ ነበር የጠበቀን። ግን ነገን የማስበውን ህልሜ እውን ለማድረግ በጣልያን ስደተኞች ካምፕ ለ 11 ወራት ቆየሁኝ።
ከኛ በፊት ወደ ጣልያን የሚገቡ ስደተኞች፡ የእጅ አሻራ ላለማድረግ እና በፖሊስ እንዳይያዙ፡በማምለጥ ነበር ወደ ሌሎች ሃገራት የሚገቡት።
አጋጣሚ እኛ እድል ስትቀናን ግን ነበረው የስደተኞች ፖሊሲ ተቀየረ።
እናም ከ 11 ወራት የስደተኞች ካምፕ ቆይታ በኋላ በህጋዊ መንገድ ወደ ጀርመን እንድገባ ተፈቀደልኝ።
አጋጣሚ ሁኖ እኔ እድል በሯን ከፍታልኝ እንጂ፡ የሰሃራ በረሃ አቋርጠው ጣልያን ከገቡ በኋላ የተጣሉ እና መጠለያ ያጡ ብዙዎች ናቸው።

የፎቶው ባለመብት, ነሽነሽ
የጀርመን ኑሮ
አሁን በምእራባዊ ጀርመን ሙንስተር ከተማ በምትገኘው ማፐን ዲ በሚባል አካባቢ እየኖርኩኝ ነው። አሁን 3 ወራት ሁኖኛል።
በጀርመን አገር ስራ ለመጀመር፡ ለ 6 ወራት የጀርመን ቋንቋ መማር ግድ ስለ ሆነ ጀርመንኛ እየተማርኩኝ ነው።
ህይወት በጀርመን እና በኤርትራ ከቶ ማወዳደር አይቻልም። የፈለግከውን የመናገር መብት አለ።
ከደጃፌ ጀምሮ አይንን የሚማርኩ ነገሮችን አያለው። በጣም ንፁህና አረንጓዴ አካባቢ ነው።

የፎቶው ባለመብት, ነሽነሽ
ሁሌ እንደምፈልገው ባላገኝም ባይሆንም ኤርትራ እያለው ዶሮ መብላት በጣም እወድ ነበር። እዚህ ግን ሁሌም በቀላሉ ዶሮ እበላለው።
እዚህ ሁኜ የሚናፍቀኝ ነገር ቢኖር ኤርትራ እያለው ያሳለፍኩት ጥሩ ጊዜ እና የአብሮ አደጎቼ ፍቅር ነው።
ለቀጣይ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ ሰላም በፌስቡክ እኣካሄድኳቸው ኣሉትን እንቅስቃሴዎች እንድሰበስባቸው እና በኤርትራ የነበረኝን የሙዚቃ ስራዎች እንድቀጥል እፈልጋለው።
ከሁሉም አንድ የምለይበት ነገር ቢኖር የአማርኛ ፊልሞች በብዛት ከማየቴ የተነሳ፡ ለማታውቀኝ የትግራይ ልጅ ተዋናይት ሰላም ተስፋየ ማፍቀሬ ነው።
በሆነ ተኣምር አሁን ካለሁበት ቦታ ነፍሴን ወደ ሌላ ኣካባቢ መላክ ብችል፡ ወደ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ባሳረፍኳት።
አዲስ አበባ ህጄ በጣም የማፈቅራት ተዋናይት ሰላም ተስፋየ በማግኘት፡ ያሉኝን የፊልም ድርሰቶች በአማርኛ እና በትግርኛ፡ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ ሰላምና ፍቅር ኣብርያት እሰራ ነበር።












