
የፎቶው ባለመብት, Reuters
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ኢራን ላለፉት 47 ዓመታት ስጋት ሆና ቆይታ የነበረ ቢሆንም “ከአሁን በኋላ ግን
አትሆንም” አሉ።
ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ለሁለት ሳምንት የሚቆይ የተኩስ አቁም ከተደረሰ በኋላ በሰጡት
ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ፒት ሄግሴት ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት ከፔንታጎን የጋራ
ወታደራዊ አዛዦች ሊቀ መንበር የሆኑት ጄነራል ዳን ኬን ጋር በመሆን ነው።
ፒት ሄግሴት "ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይህንን ቅጽበት ፈጥረዋል፤ ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ለምናለች፤
ይህንንም ሁላችንም እናውቀዋለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ሄግሰት ኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ “ታሪካዊ እና እጅግ አስደናቂ ነበር” ያሉ ሲሆን የአሜሪካ ጦር “የኢራንን ጦር አውድሟል”
ብለዋል።
ሄግሴት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም የተደረሰበትን ዕለት “ለዓለም ሰላም ትልቅ ቀን” ሲሉ አሞካሽተዋል።
አክለውም “በዓለም ግንባር ቀደም አሸባሪነትን የሚደግፍ መንግሥት ራሱን፣ ሕዝቡን ወይም ግዛቱን መከላከል ሙሉ በሙሉ አቅሙ
የለውም” ሲሉ ተናግረዋል።
ሄግሴት ዩኤስ የኢራንን ባሕር ኃይል እና አየር ኃይል ጠራርጎ ለማጥፋት የያዘችውን ወታደራዊ ዓላማ አሳክታለች - አሜሪካ
"ሰማያቸውን” ትቆጣጠራለች ብለዋል።
ኢራን የተኩስ አቁሙን የተቀበለችው “በከፍተኛ ጫና” መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰው ቴህራን የዋሺንግተንን ቅድመ ሁኔታዎች ባለትቀበል
ኖሮ “ቀጥሎ ዒላማ የሚሆኑት ድልድዮቿ፣ የኃይል ማመንጫዎቿ፣ የነዳጅ እና ኢነርጂ መሠረተ ልማቶቿ ነበሩ” ሲሉ የፕሬዚዳንት ዛቻ
ጠቅሰዋል።
ኢራን መልሶ ለመገንባት አስርታት ዓመታትን ይወስድባት ነበር በማለት የግዛቲቱ መሪዎች ይህንን በመገንዘባቸው ከስምምነት
ላይ መድረስን መርጠዋል ብለዋል።
“ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢራንን ምጣኔ ኃብት በደቂቃዎች ውስጥ ማሽመድመድ አቅም ነበራቸው ነገር ግን ርህራሄን መርጠዋል”
ሲሉ ተናግረዋል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ሚኒስትሩ የተኩስ አቁሙ “ለእውነተኛ ሰላም እና ለእውነተኛ ስምምነትን” ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመው መስሪያቤታቸው “ለአሁኑ” የበኩሉን አድርጓል ፣ ግን ኢራን እያንዳንዱን ስምምነት ማክበሯን ለማረጋገጥ ዝግጁ ይሆናል” ብለዋል ።
ሄግሴት እስራኤልን “ደፋር፣ ፈቃደኛ እና አቅም ያላትአጋር” በማለት ጠርተዋታል። የተቀረው ዓለም እና ሌሎች "የአሜሪካ አጋሮች ነን የሚሉ" አንዳንድ ማስታወሻዎችን መውሰድ አለባቸው ብለዋል።
የፔንታጎን የጋራ ወታደራዊ አዛዦች ሊቀ መንበር የሆኑት ጄነራል ዳን ኬን በበኩላቸው የአሜሪካ ጦር “ከታዘዘ ወይም ጥቃት ዘመቻውን እንዲቀጥል ጥሪ ከቀረበለት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃል ብለዋል።
“የአሜሪካ ወታደሮች ባለፉት 38 ቀናት እንዳሳየነው ፍጥነት እና ቆራጥነት የጥቃት ዘመቻውን እንድንቀጥል ከታዘዝን ወይም ከተጠራን ዝግጁ ሆነን እንጠብቃለን እና ያ እንደማይሆን ተስፋ እናደርጋለን።”