ጨቅላ ልጆቻቸውን ማጥባት ያልቻሉ እናቶችን የሚያገለግለው የእናት ጡት ወተት ባንክ

ጨቅላ ልጆቻቸውን ማጥባት ያልቻሉ እናቶችን የሚያገለግለው የእናት ጡት ወተት ባንክ

በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ጨቅላ ልጆቻቸውን ጡት ማጥባት ላልቻሉ እናቶች አገልግሎት የሚሰጥ የእናት ጡት ወተት ባንክ በናይጄሪያዋ የሌጎስ ከተማ ተቋቁሟል።

የወተት ባንኩ በሳምንት 130 ሊትር የእናት ጡት ወተት ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሽ አጥቢ እናቶች ይሰበስባል። ወተቱንም ማጥባት ለማይችሉ እናቶች እና ያለእድሜያቸው ለተወለዱ ሕጻናት በነጻ ያከፋፍላል።

በቀጣይ በሳምንት 200 ሊትር ወተት ለመሰብሰብ እና ገጠር ድረስ በመሄድ ተጨማሪ ሕጻናትን ለመርዳት ባንኩ አቅዷል።