ትራምፕን ያስቆጣውና አጋጥሞ አያውቅም የተባለው የኤፍቢአይ እርምጃ
ትራምፕን ያስቆጣውና አጋጥሞ አያውቅም የተባለው የኤፍቢአይ እርምጃ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍሎሪዳው መኖሪያ ቤታቸው ላይ የኤፍቢአይ አባላት ያደረጉት ብርበራ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎቻቸውን አስቆጥቷል።
ድርጊቱን “የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚሉት ትራምፕ፣ ባወጡት መግለጫ ፖሊስ ፍተሻውን ያካሄደው ለዋይት ሐውስ ዳግም እንዳልወዳደር እንቅፋት ለመፍጠር ነው ብለዋል።
ፍተሻው ከቀድሞ ፕሬዝዳንት የመንግሥታዊ ሰነዶች አያያዝ ጋር በተገናኘ ነው የተባለ ሲሆን፤ ፍተሻው ከዚህ በፊት በየትኛውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ ያላጋጠመ ነው ተብሏል።



