ድርጅት በመፍጠር እና መልሶ በመሸጥ የምትታወቀው ትውልደ ኢትዮጵያዊት

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
ድርጅት በመፍጠር እና መልሶ በመሸጥ የምትታወቀው ትውልደ ኢትዮጵያዊት

ኬነሳ ሙሉነህ ትውልዷ ድሬዳዋ ሲሆን፣ ዕድገቷ ደግሞ አውሮፓ ኔዘርላንድስ ነው። የቤተሰቦቿን ፍላጎት ለማሟላት ሕክምና ተምራለች። የእርሷ ፍላጎት ግን ሐኪም መሆን አልነበረም።

እናም ከተመረቀች በኋላ ድርጅቶችን እየፈጠረች ለስኬት አበቃች። በአሁኑ ወቅት ከ10 በላይ አገራት የሚሸጥ “ሙሉ” የተሰኘ ብራንድ ልብስ [የፋሽን መለያ] አላት።

ኬኔሳ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቁ ተሳታፊ ስትሆን፣ የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና የሕይወት ልምዷን በበይነ መረብ (ኦንላይን) ታስተምራለች።