የዓለማችን ኮከብ አትሌት ሞ ፋራህ ለዘመናት የደበቀውን ምስጢር ይፋ አወጣ

የዓለማችን ኮከብ አትሌት ሞ ፋራህ ለዘመናት የደበቀውን ምስጢር ይፋ አወጣ

ከዓለማችን ኮከብ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሞ ፋራህ በህፃንነቱ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መወሰዱን እና ለአስገዳጅ የጉልበት ብዝበዛ መጋለጡን ይፋ አደረገ።

በስፖርቱ ዘርፍ ለዩናይትድ ኪንግደም ባበረከተው አስተዋጽኦ በአገሪቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሆነውን ‘ሰር’ የሚለውን መለያ ያገኘው ሞ ፋራህ ስሙ በወላጆቹ የተሰጠው ሳይሆን ሐሰተኛ ነው ብሏል።

ፋራህ በህጻናት ላይ የሚደርሰውን የጉልበት ብዝባዛ ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እውነተኛ ታሪኩን ይፋ በማውጣወት ያለፈበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለቢቢሲ ተርኳል።