ውቅያኖሶች ባይኖሩ ዓለማችን ምን ልታጣ ትችል ነበር?

ውቅያኖሶች ባይኖሩ ዓለማችን ምን ልታጣ ትችል ነበር?

ከምድራችን አጠቃላይ ክፍል ውስጥ አብዛኛው በውሃ የተሸፈነ ነው። በዚህም ከአጠቃላዩ የዓለማችን ገጽታ ሁለት ሦስተኛውን የሚሸፍኑት ውቅያኖሶች ናቸው።

ውቅያኖሶች ደግሞ በውሃ የተሸፈኑ ብቻ ሳይሆኑ በውስጣቸው ለዓለማችን ሕዝብና ጠቅላላ ሥነ ምኅዳር ጠቃሚ የሆኑ እንስሳትና እጸዋትን ይዘዋል።

ውቅያኖሶች ለምንተነፍሰው አየር፣ ለዝናብ፣ ለዓለም የአየር ሁኔታ ሚዛን መጠበቅ እጅግ ጉልህ አስተዋጽኦ አላቸው። በዚህም ምድራችን ካለውቅያኖሶች ህልውናዋ ጥያቄ ውስጥ ይወድቅ ነበር።

አስኪ የውቅያኖሶችን ውለታና ያሉባቸውን ስጋቶች በአጭሩ እንመልከት?