ወጣት ሴቶች የሚሰባሰቡበት የአዲስ አበባው የ'ስኬት ቦርድ' ተጫዋቾች ቡድን

ወጣት ሴቶች የሚሰባሰቡበት የአዲስ አበባው የ'ስኬት ቦርድ' ተጫዋቾች ቡድን

እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሴቶች አዲስ አበባ ውስጥ ከተለያየ አካባቢዎች በመሰባሰብ 'ስኬት ቦርድ' በመጫወት ትርፍ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ።

የቡድኑ አባላት ወጣቶችን ለተለያዩ ጎጂ ልማዶች ከሚዳርጉ ስፍራዎች በመራቅ በስፖርቱ ከመዝናናታቸው ባሻገር፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ ስለሴቶች ያለውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር ጥረት እያደረጉ ነው።

የቡድኑ አባላት በእዚህ ጨዋታ ውስጥ በመሳተፋቸው አካላዊና አዕምሯዊ ጤና አግኝተናል ይላሉ።