ነፍሰጡር ሩሲያውያን ወደ አርጀንቲና የሚፈልሱት ለምንድን ነው?

ነፍሰጡር ሩሲያውያን ወደ አርጀንቲና የሚፈልሱት ለምንድን ነው?

በሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን ነፍሰ ጡሮች ወደ አርጀንቲና እየጎረፉ መሆናቸው ከተሳማ ሳምንታት አልፈዋል።

ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከ5 ሺህ በላይ ነፍሰ ጡር ሩሲያውያን ወደ አርጀንቲና መግባታቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ሩሲያውያኑ የደቡብ አሜሪካዊቷ አርጀንቲና ብሔራዊ ቋንቋ የሆነውን ስፓኒሽ አይናገሩም፣ ከአገሪቱ ጋርም የተለየ ግንኙነት የላቸውም። ታዲያ ለምን በዚህ ወቅት ወደ አርጀንቲና መፍለስን መረጡ?