በፕሬዝዳንት ፑቲን “ከሃዲ” የተባለው የቫግነር ቅጥረኛ ቡድን መሪ የቭገኒ ፕሪጎዢን ማን ነው?

በፕሬዝዳንት ፑቲን “ከሃዲ” የተባለው የቫግነር ቅጥረኛ ቡድን መሪ የቭገኒ ፕሪጎዢን ማን ነው?

የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊዎች ቫግነር ቡድን መሪ የቭገኒ ፕሪጎዢን ለአንድ ቀን የቆየ አመጽ በሩሲያ ጦር ላይ ካካሄደ በኋላ ወደ ቤላሩስ ተሻግሮ ለመኖር ወስኗል።

በተለያዩ አገራት የሚንቀሳቀሰው ቫግነር ቡድን፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ነበረው።

የቡድኑ መሪ ፕሪጎዢን ከፕሪዝዳንት ፑቲን ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ነበረው። አሁን ግን “ከሃዲ” ተብሏል።