ሐሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች በአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የደቀኑት አደጋ
ሐሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች በአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የደቀኑት አደጋ
የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት የመጡ ስደተኞች ላይ ከፍ ያለ ጥላቻ ተፈጥሯል።
በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት በመጡ ስደተኞች ላይ ጥላቻ እንዲፈጠር እና እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ሐሰተኛ ወሬዎች እና ቪዲዮዎች እየተሰራጩ ነው።
ይህንን ተከትሎም በቱኒዚያ ፀረ ስደተኞች ተቃውሞዎች እያካሄዱ ሲሆን፣ ለዜጎቻቸው ደኅንነት የሰጉ አንዳንድ አገራትም በስደት ላይ ያሉ ዜጎቻቸውን ከቱኒዚያ እያስወጡ ነው።
ቱኒዚያ ውስጥ ከሰሃራ ካሉ የአፍሪካ አገራት የመጡ ስደተኞችን በሚመለከት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሚዘዋወሩ ቪዲዮዎች ዙሪያ ቢቢሲ ምርመራ አድርጎ እውነታው የተለየ መሆኑን ተረድቷል።



