እስካሁን ሴት መሪዎች ከፍተኛ የሥልጣን መንበርን የያዙባቸው አገራት የትኞቹ ናቸው?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
እስካሁን ሴት መሪዎች ከፍተኛ የሥልጣን መንበርን የያዙባቸው አገራት የትኞቹ ናቸው?

ያደጉ እና ዴሞክራሲያዊ የሚባሉትን አገራት ጨምሮ በመላው ዓለም በመሪነት ቦታ ላይ የሚገኙ የሴቶች ቁጥር አሁን ድረስ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው።

በአገራት ፖለቲካ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ተመጣጣኝ እንዲሆን ማድረግ ዘወትር የሚነሳ ጉዳይ ቢሆንም አሁንም ከሚጠበቀው ደረጃ በታች ነው።

ኃያሏን አሜሪካን ጨምሮ በዘመናዊው የዓለም ታሪክ ውስጥ ወሳኝ በሆነው የአገር መሪነት ሥልጣን ላይ በመውጣት የሚጠቀሱ ሴቶች ቁጥር ውስን ነው።

ለመሆኑ ሴቶች የመሪነት ሥልጣንን የያዙባቸው አገራት የትኞቹ ናቸው?