ዩሮ 2024፡ የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ውጤት ግምት

የቢቢሲ የእርግ ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የመጀመሪያው ዙር ግጥሚያዎች ያልጠበኳቸው ውጤቶች ተመዝግበዋል ይላል።

ሱተን ከ12ቱ ጨዋታዎች የሰባት ጨዋታዎች አሸናፊውን በትክክል ገምቷል። ስሎቫኪያ በቤልጂዬም ላይ ያሳካችው ድል እንዲሁም ሮማኒያ ሳይጠበቅ ዩክሬንን ያሸነፈችበት አጋጣሚ ጨርሶ ያልጠበኩት ነው ይላል።

በሁለተኛው ዙር ስፔን ከ ጣሊያን እንዲሁም ኔዘርላንድስ ከ ፈረንሳይ የሚገናኙባቸው ጨዋታዎች የሚጠበቁ ናቸው።

ሱተን ከረቡዕ ሰኔ 12 እስከ 15/ 2016 ዓ.ም. የሚደረጉ የ12 ጨዋታዎች ግምትን እንደሚከተለው አስቀምጧል።

ረቡዕ ሰኔ 12

ጀርመን ከ ሃንጋሪ

ግምት፡ 3 - 0 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 2 - 0)

ስኮትላንድ ከ ስዊትዘርላንድ

ግምት፡ 1 - 2 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 1)

ክሮሺያ ከ አልባኒያ

ግምት፡ 1 - 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 2 - 2)

ሐሙስ ሰኔ 13

ስሎቬኒያ ከ ሰርቢያ

ግምት፡ 1 - 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 1)

ዴንማርክ ከ እንግሊዝ

ግምት፡ 0 - 2 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 1)

ስፔን ከ ጣሊያን

ግምት፡ 2 - 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 0)

አርብ ሰኔ 14

ስሎቫኪያ ከ ዩክሬን

ግምት፡ 1 - 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 2)

ፖላንድ ከ ኦስትሪያ

ግምት፡ 0 - 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 3)

ኔዘርላንድስ ከ ፈረንሳይ

ግምት፡ 1 - 2 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 0 - 0)

ቅዳሜ ሰኔ 15

ጆርጂያ ከ ቼክ

ግምት፡ 0 - 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 1 - 1)

ቱርክ ከ ፖርቹጋል

ግምት፡ 0 - 2 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 0 - 3)

ቤልጂዬም ከ ሮማኒያ

ግምት፡ 2 - 1 (ጨዋታው የተጠናቀቀበት ውጤት 2 - 0)