ቻይናውያን ወጣቶች ልጅ መውለድ አለመፈለግ ያስከተለው የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል

ቻይናውያን ወጣቶች ልጅ መውለድ አለመፈለግ ያስከተለው የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል

ቻይና ለረጅም ጊዜ በጥብቅ ተግባራዊ ስታደርገው የነበረው አንድ ቤተሰብ አንድ ልጅ የሚለው ፖሊሲዋ በሕዝብ ቁጥር እድገቷ እና ስብጥር ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማሳደሩ ለውጥ ለማድረግ ተገዳለች።

ይህ የአንድ ልጅ ፖሊሲ ተነስቶ ቤተሰብ ተጨማሪ ልጅ እንዲኖረው ቢፈቀድም የቻይና የሕዝብ ቁጥር ግን እየቀነሰ ነው።

በዚህም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በሕዝብ ብዛት የዓለማችን ቀዳሚ አገር የነበረችው ቻይና፣ በሕንድ ተቀድማ የሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ለዘመናት ጥንዶች የሚኖራቸውን የልጆችን ቁጥር በአንድ እንዲወስኑ መደረጉ ስር ሰዶ አሁን በርካታ ቻይናውያን ወጣቶች ፈጽሞ አለመውለድን ይመርጣሉ። ለምን?