የ10 ሺህ ሰዎች አንጎል የተከማቸበት የዴንማርክ የሥነ አዕምሮ ምርምር ተቋም
የ10 ሺህ ሰዎች አንጎል የተከማቸበት የዴንማርክ የሥነ አዕምሮ ምርምር ተቋም
የደቡብ ዴንማርክ ዩኒቨርሲቲ 10 ሺህ የሚጠጉ በዓመታት ሂደት ውስጥ የተሰበሰቡ የሰው ልጅ አንጎሎችን አከማችቷል።
እነዚህም በአዕምሮ ጤና ዙሪያ ለሚደረጉ ጥናት እና ምርምሮች እንዲረዳ በሚል ከ1940ዎቹ ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ ድረስ ለአራት አስርት ዓመታት የተሰበሰቡ ናቸው።
የዚህ ስብስብ ብዛት በዓለም ላይ ካሉት ቀዳሚው የሰው ልጅ አንጎል ክምችት እንደሆነ ይታመናል።
የሕክምና ሙያተኞች እንደሚሉት እነዚህ አንጎሎች ያለሕሙማኑ ፈቃድ የተሰበሰቡ ቢሆኑም፣ ከዕድሜ ጋር በሚከሰቱ እና በሌሎች የአዕምሮ ጤና እክሎች ላይ ለሚደረጉ ምርምሮች ጠቃሚ ሆነዋል።



