ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቸኳይ ስብሰባ የጠሩበት በዩኬ የተቀጣጠለው ፀረ ስደተኞች አመጽ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቸኳይ ስብሰባ የጠሩበት በዩኬ የተቀጣጠለው ፀረ ስደተኞች አመጽ
በዩናይትድ ኪንግደም ባለፈው ሳምንት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በበርካታ የአገሪቱ ከተሞች ውስጥ ተባብሶ ቀጥሏል።
ስደተኞችን እና ሙስሊሞችን ኢላማ ባደረገው ተቃውሞ በንብረት እና በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ደርሷል።
አመጹን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቀኝ አክራሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ ለመምከር ካቢኔያቸውን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።



