"አሜሪካ ጋዛን በመቆጣጠር መልሶ የመገንባት እና ፍልስጤማውያንም ሌላ ቦታ የማስፈር ሃሳብ አላት" ፕሬዝዳንት ትራምፕ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
"አሜሪካ ጋዛን በመቆጣጠር መልሶ የመገንባት እና ፍልስጤማውያንም ሌላ ቦታ የማስፈር ሃሳብ አላት" ፕሬዝዳንት ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ነዋሪዎች ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ እና አሜሪካ አካባቢውን ከፍርስራሽ እና ካልፈነዱ የጦር መሳሪያዎች በማጽዳት መልሶ የመገንባት ሃሳብ እንዳላት ተናገሩ።

ትራምፕ ዋሽንግተን ውስጥ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ይህንን ሃሳባቸውን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እነደደገፉት ገልጸዋል።ነገር ግን የአካባቢው አገራት የዶናልድ ትራምፕን ሃሳብ እየተቃወሙት ነው።