በየትኞቹ የዓለም አገራት ውስጥ በርካታ የጦር መሣሪያዎች በተራ ዜጎች እጅ ይገኛል?
በየትኞቹ የዓለም አገራት ውስጥ በርካታ የጦር መሣሪያዎች በተራ ዜጎች እጅ ይገኛል?
በመላው ዓለም ከአንድ ቢሊዮን በላይ የጦር መሣሪዎች ይገኛል። ብዙዎቹ የሚገኙት ደግሞ በተራ ሰዎች እጅ ነው።
በአሜሪካ ዘወትር በዜና እንደሚዘገበው የታጠቁ ሰዎች በርካታ ሰዎችን በጅምላ ይገድላሉ። ለዚህም ምክንያቱ የጦር መሳሪያ እንደልብ መገኘቱ እንደሆነ ይነገራል።
አሜሪካ ውስጥ በታጣቂዎች ከሚፈጸሙት የጅምላ ግድያዎች በላይ በጦር መሳሪያ የሚፈጸመው እራስን ማጥፋት በእጅጉ የበዛ ነው።
አንዳንድ አገራት ልል የጦር መሣሪያ ቁጥጥር አላቸው። ውስን አገራት ደግሞ ከፍተኛ ቁጥጥር ያደርጋሉ፤ በዚህ ረገድ ጃፓን ተጠቃሽ ነች።
ለመሆኑ የትኞቹ አገራት ውስጥ ከፍተኛው የጦር መሳሪያ መጠን በተራ ዜጎች እጅ ይገኛል?



