“ወደ አገር መመለስ እስካልተቻለ ድረስ ምን ነጻነት አለ?”- በስደት ላይ የሚገኙ የቢቢሲ ጋዜጠኞች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, “ወደ አገር መመለስ እስካልተቻለ ድረስ ምን ነጻነት አለ?”- በስደት ላይ የሚገኙ የቢቢሲ ጋዜጠኞች
“ወደ አገር መመለስ እስካልተቻለ ድረስ ምን ነጻነት አለ?”- በስደት ላይ የሚገኙ የቢቢሲ ጋዜጠኞች

ከአራት ዓመታት በፊት ከነበረው አኃዝ ጋር ሲነጻጸር ከአገራቸው ተሰደው የሚሠሩ የቢቢሲ ጋዜጠኞች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። እንደ ኢራን፣ ሩሲያ እና አፍጋኒስታን በመሳሰሉት አገራት በመንግሥት ተሳደው ከአገራቸው ውጭ የሚሠሩ የቢቢሲ ጋዜጠኞች ቁጥር 310 ደርሷል።

እንደ ኢራን ባሉ አገራት የሚገኙ ጋዜጠኞች ደግሞ ከአስር ዓመታት በላይ በግዞት አሳልፈዋል። ብዙዎቹም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል ወይም የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል።