ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች

ከሁለት ሳምንት በፊት ሦስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት 26 ኢጲስ ቆጶሳትን ከሾሙ በኋላ የተከሰተው ችግር ተባብሶ አሁን ላይ ደርሷል።

የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ሹመት የሰጡትን እና የተቀበሉትን አውግዞ እንዲለዩ ሲወስን፣ እነሱም በበኩላቸው ውሳኔውን እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

ውዝግቡ በተባባሰበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰነዘሩት ሃሳብ ከቤተክርስቲያኗ ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞት ችግሩ ሌላ ገጽታ እንዲይዝ አድርጎታል።

ይፋዊ ተቃውሞ ግጭት፣ ሞት፣ የአካል ጉዳት እንግልት እና አስር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ተከስተዋል። በዚህ ሳምንትም ውጥረቱን የሚያረግብ ነገር አስካሁን አልታየም። ባለፉት ቀናት የተከሰቱ ዋነኛ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?

ደግሞ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ እነዚህን ጳጳሳትንና የሾሟቸውን ኤጲስ ቆጶሳት አውግዞ ለይቷቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጉዳዩ ላይ ሃሳብ ሰጥተው ሲኖዶሱ ሃሳባቸውን "ወገንተኛ" ብሎታል። ሌሎች ጉዳዮችስ ምን ይመስላሉ?