ከቤት እመቤትነት ወደ ዝነኛ የቅርጽ ተወዳዳሪነት የተሸጋገረችው ኔፓላዊት
ከቤት እመቤትነት ወደ ዝነኛ የቅርጽ ተወዳዳሪነት የተሸጋገረችው ኔፓላዊት
ኔፓላዊቷ ራጃኒ ሽሪስታ የሰውነት ቅርጽ ስፖርት ተወዳዳሪ መሆኗ የባሏን እናት ጨምሮ ብዙ የአካባቢዋን ሰዎች አስገርሟል።
አንዳንዶች የሴት ልጅ ሰውነት ለስላሳ መሆን እንዳለበት በመግለጽ ጡንቻ ማፈርጠሟን እንድታቆም መክረዋታል።
ራጃኒ ግን በውሳኔዋ ጸንታ በ2017 (እአአ) ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች።



