‘እየሱስን ለማግኘት’ ጾም ላይ የቆዩ 100 የሚጠጉ ሰዎች አስከሬን የተገኘበት ስፍራ

‘እየሱስን ለማግኘት’ ጾም ላይ የቆዩ 100 የሚጠጉ ሰዎች አስከሬን የተገኘበት ስፍራ

እየሱስን ለማግኘት እራሳቸውን በጾም አድክመው እንዲሞቱ በሚያበረታታ የእምነት ቡድን ስብከት የተነሳ የሞቱ ወደ 100 የሚደርሱ ሰዎች አስከሬን በምሥራቅ ኬንያ ተገኝቷል።

አሁንም በዚሁ ስፍራ ከሃይማኖታዊው ትዕዛዝ አናፈነግጥም ብለው በርካታ ሰዎች በጾም ላይ እንደሚገኙ ፖሊስ አስታውቋል። በዚህም ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል።

የኬንያ መንግሥትም በእንዲህ አይነቱ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ዙሪያ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት እየተደረገበት ነው።