ለንጉሥ ቻርለስ የንግሥና ሥነ ሥርዓት የተዘጋጁት ወርቃማ ሰረገላዎች
ለንጉሥ ቻርለስ የንግሥና ሥነ ሥርዓት የተዘጋጁት ወርቃማ ሰረገላዎች
የንጉሥ ቻርለስ ሦሰተኛ የንግሥና ሥነ ሥርዓት ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 ዓ.ም. በታላቅ ዝግጅት ለንደን ውስጥ ይከናወናል።
ንጉሡ እና ባለቤታቸው በዓለም ዕድሜ ጠገብ በሆኑ ወርቃማ ሰረገላዎች ላይ ሆነው ሥነ ሥርዓቱ ወደሚካሄድበት ቦታ ይሄዳሉ።
በይፋ ንግሥናቸውን ከተቀበሉ በኋላም ወደ ባኪንግሃም ቤተ መንግሥት በልዩ ሥነ ሥርዓት ሲመለሱም በሰረገላዎቹ ተሳፍረው ይሆናል።
እነዚህ ልዩ ሰረገላዎች ከአውሮፓውያኑ 1830ዎቹ ጀምሮ በተከናወኑ በእያንዳንዱ የንግሥና ሥነ ሥርዓቶች ላይ ያገለገሉ እጅግ የተዋቡ ሰረገላዎች ናቸው።



