ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ቁጣን ከቀሰቀሰው ጾታዊ ጥቃት የተረፉት ሴቶች ምስክርነት
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ቁጣን ከቀሰቀሰው ጾታዊ ጥቃት የተረፉት ሴቶች ምስክርነት
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሙዚቃ ቪዲዮ ክሊፕ በመስራት ላይ የነበሩ የአንድ ቡድን ሴት አባላት በታጠቁ ሰዎች በቡድን የመደፈር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
ታጣቂዎቹ የቡድኑን ወንድ አባለት ዘርፈው ከደበደቡ በኋላ ነበር በሴቶቹ ላይ አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙት። ይህም በመላዋ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ቁጣን ቀስቅሷል።
ጥቃቱን ተከትሎ ፖሊስ 130 ሰዎችን አስሯል። ታሳሪዎቹ ሰነድ አልባ ስደተኞች ናቸው። የተደፈሩት ሴቶች ሞተዋል ተብለው ጉድጓድ ውስጥ ቀብረዋቸውም እንደነበር ይናገራሉ።
ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ሴቶች መካከል የተወሰኑት የገጠማቸውን ለቢቢሲ ተናገረዋል።



