እናቱን ለመርዳት ለጉልበት ብዝበዛ የተጋለጠው ኢትዮጵያዊ ታዳጊ
በርካታ ሕጻናት በድህነት ምክንያት የቤተሰባቸውን ገቢ ለመደጎም ሲሉ በተለያዩ ከባድ የጉልበት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
በዚህም በተለያዩ አገራት የሚገኙ ታዳጊዎች ለጉልበት ብዝበዛ ተዳርገው ከእድሜያቸውና ከአቅማቸው በላይ ለሆነ ጫና ይዳረጋሉ።
ኢትዮጵያም የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ አስከፊ ከሆነባቸው አገራት መካከል ትገኛለች ።
በኢትዮጵያ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት ለጉልበት ብዝባዛ የሚዳርጉ ሥራዎችን እንዳይሰሩ በሕግ ቢደነገግም፣ 60 በመቶ የሚሆኑት ልጆች ሥራ የሚጀምሩት በ11 ዓመታቸው ነው።
ይህ ቪዲዮ አንድ ታዳጊ እናቱን ለመርዳት ሲል የሚያከናውን ሥራ ያሳያል።









